ለናይጄሪያዊያን ዜጎች ነፃ የአየር ጉዞ ተዘጋጀ

0
986

በደቡብ አፍሪካ ለሚኖሩ እና ሰሞኑን በመጤ ጠል ጥቃት ቀዳሚ የጥቃቱ ዒላማ ለሆኑት ናይጄሪያ ዜጎች ወደ አገራቸው የሚመለሱበት ነፃ የአየር ጉዞ መዘጋጀቱ ታወቀ። በደቡብ አፍሪካ ከሰሞኑ በተቀሰቀሰው አለመረጋጋት በርካታ የውጭ አገር ዜጎች ህይወታቸው እና ንብረታቸው እንደጠፋ በርካታ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች ሲዘግቡት ሰንብተዋል።

በናይጄሪያዊያን ላይ የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎም በርካታ ናይጄሪያዊያን በዋና ከተማቸው ቡጃ ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን፣ በደቡብ አፍሪካ ዜግነት ባላቸው ግለሰቦች የሚተዳደሩ የንግድ ተቋማት ላይም ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል።

አገሪቱ ፖሊስ ኹከቱን ለማብረድ ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል። በደቡብ አፍሪካ የተከሰተውን መጤ ጠል ጥቃት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሬ ራማፎዛ በይፋ አውግዘዋል። ይህንም ተከትሎ ሦስት የአፍሪካ አገራት መሪዎች ተቃውሟቸውን በደቡብ አፍሪካ የሚካሔደውን የዓለም ኢኮኖሚ ጉባኤ ባለመሳተፍ ገልፀዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 44 ጳጉሜ 2 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here