ዳሰሳ ዘ ማለዳ ሐሙስ ነሐሴ 30/2011

0
844

1-የአውሮፖ ኅብረት የኢትዮጵያ ቡና ገበያ በዓለም አቀፉ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆን የሚያስችል የ15 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉ ታዉቋል።ህብረቱ አቋርጦት የነበረዉን ድጋፍ እንደ አዲስ መጀመሩ በቡና ዉስጥ ያለዉን ችግር ከመቅረፉ ባሻገር የቡናን ምርታማነት እና የተሻለ የቡና ዝርያ ለማሰራጨት ከፍተኛ ሚና እንዳለዉ ተነግሯል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)

 

………………………………………………………………

 

2­-የወጪ ንግድ ውል ላይ ክህደት በሚፈፅሙ ነጋዴዎች ላይ ሕጋዊ ዕርምጃ እንደሚወሰድ የኢፌዲሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………….

3- ተሸከርካሪዎች የ3ኛ ወገን የመድኅን ሽፋን እንዲኖራቸው ከመስከረም 01/2012 ዓ.ም ጀምሮ ሕግን የማስከበር ተግባር ሊጀመር መሆኑ ታዉቋል፡፡በ2005 ዓ.ም የተቋቋመው የመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ በዋናነት የመድህን ሽፋን የሌላቸው ሁሉም ተሽከርካሪዎች የመድኅን ሽፋን እንዲኖራቸው እና በትራፊክ አደጋ ሞት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት የደረሰባቸው አካላት ካሳ እና ህክምና እንዲያገኙ  የሚያስችል ነዉ፡፡(ኤዜአ)

………………………………………………………………

4-በጋምቤላ ክልል ነሐሴ 30/2011 ኹለት የግብረ-ሰናይ ድርጅት ሰራተኞች ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን የአይን እማኞች እና የክልሉ መንግሥት ሰራተኞች ተናግረዋል። በጋምቤላ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰራተኛ የሆኑ አንድ የአይን እማኝ እንዳሉት ሰራተኞቹ የተገደሉት “ዊኜል” ከተባለ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ለመድረስ ጥቂት ሲቀራቸው መሆኑን ተናግረዋል።አክሽን አጌይንስት ኸንገር (Action Against Hunger) የተባለ ዓለም አቀፍ ተቋም ተቀጣሪ ናቸው የተባሉት ኹለት ሰዎች «ወደ ኢታንግ ከሚወስደው መንገድ ተገንጥለው ወደ ስደተኞች መጠለያለው ለመግባት ወደ ስድስት ኪሎ ሜትር ሲቀራቸው» በታጣቂዎች መገደላቸውን የአይን እማኙ አብራርተዋል።(ዶቼ ቬለ)

………………………………………………………………

5–በአዲስ አበባ ከተማ በ2011 በጀት አመት ባሉት መንገዶች ላይ በተሽከርካሪዎች ግጭት ምክንያት ብቻ ከ 9 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር  በላይ የሚገመት የመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።በበጀት ዓመቱ 12 ወራት ውስጥ 310 ግጭቶች በቀለበት መንገድ በሚገኙ ሀብቶች ላይ ሲደርስ 584 ግጭቶች ደግሞ ከቀለበት መንገድ ውጪ በድምሩ 894 የግጭት አደጋዎች  መድረሳቸውን ነው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን አስታዉቋል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)

 

………………………………………………………………

6- የመንግሥት ፖሊሲ ማስፈጸሚያ የሆኑት የኢትዮጵያ ልማት ባንክና የኢትዮጵ ንግድ ባንክ ጥልቅ ማሻሻያ እያደረጉ መሆኑን አስታዉቀዋል።የሚደረገው ማሻሻያ መንግስት በቀጣይ 3 ዓመታት የሚተገብረው የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ አካል እንዲሆን ተደርገዋል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)

………………………………………………………………

7- በቴክኖሎጂ የተደገፈ የእንስሳት ሀብት ልማት ፕሮጀክት በኦሮሚያ ክልል ተጀመረ። ፕሮጀክቱ በክልሉ ያለውን ወተትና የሥጋ ሀብት በስድስት እጥፍ እንደሚያሳድገው ተገምቷል። (አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………………

8-  የሐረር ሜትሮ ታክሲ ማኅበር ለነዳጅ ማደያ ተሰጣቸው ቦታ መከላከያ የእኔ ነው በማለቱ ግንባታው እንደተስተጓጎለ አስታወቁ። (ዶቼ ቬለ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here