በኦሮሚያ ክልል አዲስ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሊገነባ ነው

0
756

የኦሮሚያ ኢንዱስትሪያል ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በወለጋ ዞን የአግሮ ኢንዱስተሪያል ፓርክ ሊገነባ ነው፡፡ አግሮ ኢንዱስትሪያል ፓርኩን ለማስገንባት የቦታ መረጣ እና የአዋጭነት ጥናት ለማከናወን በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ ኢንዱስትሪያል ፓርኩ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ የግብርናውን ዘርፍ ግብዓቶችን በማቅረብ የሚያግዝ ሲሆን በግብርና ምርቶች ላይ ዕሴት በመጨመር በምግብ ራስን ለመቻል እንዲሁም ለኢኮኖሚያዊ እድገት ትልቅ ሚና እንደሚኖራችው ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል ሲል አስታውቋል፡፡

በአካባቢው ለሚገኙ አርሶ አደሮችም ምርታቸውን ለገበያ ከማቅረብ ባሻገርም የገበያ ትስስር ለመፍጠር ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል። በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ክልሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ከሚያስገነባቸው ውጭ በፌደራል መንግስት ወጪ የተገነቡ በቅርቡ የሚገነባውን የአዳማ ቁጥር ኹለት የኢንዱስትሪ ፓርክ ጨምሮ ቁጥራቸው ወደ አራት ከፍ ይላል።

ቅጽ 1 ቁጥር 44 ጳጉሜ 2 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here