መንግሥት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ መኪኖችን ሊገዛ ነው

0
429

የመንግሥት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የተሸከርካሪ ግዢ ፍላጎት ላቀረቡ የፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያገለግሉ 468 ተሽከርካሪዎችን በመጪው ወር መጀመሪያ ለመግዛት ዝግጅቱን አጠናቀቀ።

በግዢና ንብረት ማስወገድ በኩል የሚደረገው የተሸከርካሪ ግዢ መንግሥትን ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ሊያደርግበት ይችላልም ተብሏል።
የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ አቅም ያላቸውን 24 ባለ 6 ሲሊንደር አምቡላንሶች፣ 159 ፒካፖች፣ 61 ሰው የመያዝ አቅም ያላቸው 128 አውቶቡሶችን እና 10 የውሃ ቦቴዎች እንዲገዙለት ጠይቋል።

የአገልግሎቱ የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ አሰፋ ሰለሞን ለአዲስ ማለዳ እንደገለፁት የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ 16 ባለኹለት ጋቢና ፒክ አፕ መኪና እንዲገዛለት ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን በግብርና ሚኒስቴር የብሔራዊ እንስሳት ጤና ምርምርና ጥናት ማዕከል አንድ አውቶቡስ ጥያቄ አቅርቧል።

በተመሳሳይ የኢምግሬሽን ዜግነት የወሳኝ ኩነት ኤጀንሲም በበኩሉ 11 ሚኒባሶች እንዲገዙለት ጠያቄ ያቀረበ ሲሆን በአጠቃላይም ተቋማቱ ያለባቸውን የተሸከርካሪ እጥረት ከግምት ውስጥ በማስገባት ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ጨረታውን ለማከናወን የሰነድ ማዘጋጀት ሥራዎች ተጠናቀዋል።
ጨረታው የአገር ውስጥ እና ዓለማቀፍ ኩባኒያዎችን የሚያሳትፍ ይሆናል ተብሎ ያጠበቃል።

ከዚህ ቀደም መገቢት 2010 በተደረገው የተሸከርካሪ ግዢ ላይ በላይ አብ ሞተርስ 400 ተሸከርካሪዎችን ለማቅረብ 352 ሚሊዮን ብር በማቅረብ ከመንግሥት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጋር ውል ተፈራርሞ ማቅረቡ ይታወሳል።

በወቅቱም ስምንት-ሲሊንደር ተሽከርካሪዎች ለሚኒስትሮች፣ ለክልል ሚኒስትሮች፣ ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፕሬዚዳንቶች እና ለምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ ለኮሚሽነሮች እና ለምክትል ኮሚሽነሮች የተያዙ ሲሆን ስድስት እና አራት-ሲሊንደር ተሽከርካሪዎች የመስክ አገልግሎት ዳይሬክተሮች የሚጠቀሙባቸው ነበሩ። .

የመንግሥት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎቱ በ2011 በጀት ዓመት ለተሽከርካሪ ግዥ በብር 9 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ገደማ ወጪ

ማድረጉ ይታወሳል።

ቅጽ 1 ቁጥር 44 ጳጉሜ 2 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here