ነፃነት ለተጋሩ የፖለቲካ እስረኞች ዓለም አቀፍ ንቅናቄ መግለጫ አወጣ

0
636

የትግራይ ሕዝብ የተቃጣበትን ዘመቻና የዘር ጥቃት ለመመከት የሚል ሃሳብ የሚያስተጋባው ነፃነት ለተጋሩ የፖለቲካ እስረኞች ዓለም አቀፍ ንቅናቄ እሁድ ጳጉሜ 3/2011 በአዲስ አበባ አክሱም ሆቴል አስተባባሪዎች መግለጫ ሰጥተዋል።  ከአስተባባሪዎች ውስጥ ፍፁም ብርሐኔ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት በአዲስ አበባ ብቻ ከ3መቶ በላይ የሚሆኑ ተጋሩ ያለ በቂ ምክንያት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እና በፍርድ ቤት ጉዳያቸው እየታየ እንደሆነ የጠቀሱ ሲሆን ፥ በክልሎችም በርካቶች በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤትም እየቀረቡ እንዳልሆነ አስታወቀዋል። ፍፁም ቀጥለውም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ በርካታ ተጋሩ  ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ከኹለትና ሦስት ወራት በላይ ታስረው እንደሚገኙ ጨምረው ገልጸዋል።

በመግለጫው እንደተገለፀው፤ ባለፉት 15 ወራት የትግራይ ተወላጆች በዘራቸው ተለይተው ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን ጠቅሰው በተለያዩ ድብቅ እስር ቤቶች የሚገኙ ተጋሩ በአስቸኳይ እንዲፈቱ አሳስቧል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ገለልተኛ እና ውጭ አጣሪ ቡድን ወደ አገር ውስጥ በመግባት በትግረዋይ ላይ እየተካሔደ ያለውን ጥቃት እንዲያጣራ እና በዚህ እኩይ ተግባር ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች፣ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ የሚዲያ አካላት ተጠያቂ የሚሆኑበትን መንገድ እንዲፈጠር ጥሪ አቅርቧል።

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here