አምባሳደር ስለሺ በቀለ ከሚሲዮኑ ዲፕሎማቶችና ሰራተኞች ጋር ትውውቅ አደረጉ

0
1596

ዕረቡ ሚያዚያ 26 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በአሜሪካ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ስለሺ በቀለ ከዋሽንግተን ዲሲ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች እና ሰራተኞች ጋር ትውውቅ አድርገዋል።

በዕለቱ አምባሳደር ስለሺ እንደገለጹት የሚሲዮኑ ባልደረቦች ዋና ትኩረት ዘመናትን ያስቆጠረው የኹለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የበለጠ እንዲሻሻል ኹሉን አቀፍ ጥረት ማድረግ ላይ ይሆናል።

በዳያስፖራ ተሳትፎ፣ ህዝብ ለህዝብ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ንግድና ኢንቨስትመንት፣ ገጽታ ግንባታ፣ ቱሪዝምና በሌሎች ዘርፎች ያለውን ትብብር ማጎልበት እንደሚገባም ገልጸዋል።

የሚሲዮኑ ባልደረቦች በበኩላቸው የአገራቱ ግንኙነት ዘመናትን ያስቆጠረውን ዲፕሎማሲያዊ መስተጋብር የሚመጥን እንዲሆን ከመቼውም ጊዜ በላይ በሙሉ አቅም እንደሚሰሩ መናገራቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
_____
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here