ዳሰሳ ዘማለዳ ረቡዕ ጷጉሜ 6/2011

0
703
  • በርካታ ሐኪሞችን፣ ነርሶችን፣ የላብራቶሪ ባለሙያዎችን እና የመስክ የጤና መኮንኖችን ያካተተ ቡድን የችጉንጉኒያ ወረርሽኝ በስፋት ወደ ታየባት ድሬዳዋ ከተማ ዛሬ ጳጉሜ 6/2011 አቅንቷል። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………………….

  • መስከረም 1 /2012 የሚከበረውን ኢትዮጵያን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ የኃይል ፍላጎት ሊጨምር ስለሚችልና የድንጋይ ወፍጮ፣ የብረታ ብረት፣ የጨርቃ ጨርቅ፣ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ የሲሚንቶ፣ የፕላስቲክ፣ የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓት ፋብሪካዎች ከዛሬ ጷጉሜ 6/2011 ከንጋቱ 12 ሰዓት እስከ መስከረም 1/ 2012 ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ ከዋናው የኃይል ቋት /ከግሪድ/ የሚያገኙት ኃይል እንደሚቋረጥ የኢትዮጵያ ኢሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል። (አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………

  • የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዐስር ኤር ባስ ኤ350 አውሮፕላኖቹ ላይ የሳተላይት ኢንተርኔት አገልግሎትን ተግባራዊ አድርጓል። መንገደኞች በገንዘብ ወይም ባላቸው ሼባ ማይልስ መጠን መግዛት እንዲችሉ ሁኔታዎች የተመቻቹ ሲሆን 100 ሜጋ ባይት በ10 ዶላር ወይም በ4ሽ ማይል እና 200 ሜጋ ባይት ደግሞ በ20 ዶላር ወይም 8ሽሕ ማይል ዋጋ ተቆርጦለታል።(አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………………………….

  • አዲሱ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ርስቱ ይርዳው የደቡብ ክልል ሕዝቦች በየአካባው የተደራጁትን ‹‹የጎበዝ አለቆች›› እንዳይከተል በፅኑ አሳስበዋል። (ዶቼ ቬለ)

………………………………………………………….

  • በዘመን መለወጫ በዓል ላይ ደንበኞች የውሃ ችግር እንዳያጋጥማቸው እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታወቀ።ከጷጉሜ 1 እስከ መስከረም 5 የሚቆይ በማዕከል እና በስምንቱም ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ጊዜያዊ ኮሚቴ በማቋቋም እስከ ምሽቱ 5 ሰዓት ድረስ እየሰራሁ ነው ብሏል ባለስልጣኑ፡፡የውሃ እጥረቱን ለመቅረፍ እንዲቻል በየዕለቱ 14 ሺሕ ሜትር ኪዩብ ተጨማሪ ውሃ እየተመረተ እንደሚገኝም ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡(ኤዜአ)

………………………………………………………

  • በመጪው ዓመት 2012 የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር 21 ሽሕ የቀንድ ከብቶችን ለማዳቀል ማሰቡን ገለጸ። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………………

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here