በቡራዩ ከተማ ውስጥ የቦንብ ጥቃት ደረሰ

0
577

መስከረም 1/2012 በቡራዩ ከተማ ማታ አንድ ሰዓት ላይ ዘጠኝ የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት ላይ የቦንብ ጥቃት መድረሱ ተገለጸ። በጥቃቱ ቀላል የአካል ጉዳት አጋጥሟል። የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን እንዳስታወቀው የጥቃቱ አድራሾች ሽፍቶች እንደሆኑ ጥርጣሬውን ግልፅ ያደረገ ሲሆን ተጠርጣሪዎች ተይዘው በምርመራ ላይ እንደሚገኙም አስታውቋል።

በቦንብ ጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው የፖሊስ አባላት በፖሊስ ሆስፒታል የሕክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን አንድ የፖሊስ አባል ሕክምናውን ተከታትሎ ወደ ቤቱ መመለሱንም ታውቋል። በጥቃቱ የመቁሰል አደጋ ከደረሰባቸው ግለሰቦች ውስጥ የፖሊሶች ምግብ አብሳይ ይገኙበታል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here