የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የፊታችን እሁድ ከመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ለመወያየት ማቀዱን ይፋ አደረገ። ውይይቱ በፓርቲው አላማ እና አገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያውጠነጥን ሲሆን በመቐለ ከተማ አስተዳደር አዳራሽ ይካሄዳል።
ፓርቲው ሊሰራቸው ያሰባቸውን አገራዊ ጉዳዮችና ተግባራት በውይይቱ ወቅት ይፋ የሚደረግ ሲሆን የፓርቲው አመራሮች የሆኑት አንዱአለም አራጌ እና የሺዋስ አሰፋ እንዲሁም የክልሉ የኢዜማ አመራሮች ስብሰባውን ይመሩታል ተብሎ ይጠበቃል።
ቅጽ 1 ቁጥር 45 መስከረም 3 2012



