ሲፒጄ ኤርትራ በዓለም አንደኛ የሚድያ አፈና ፈፃሚ መሆኗን አስታወቀ

0
983

የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪው ሲፒጄ ባወጣው ዘገባ ኤርትራ በዓለም አንደኛ የሚድያ አፈና ፈፃሚ ስትሆን ሰሜን ኮርያ ሁለተኛ፣ እንዲሁም ቱርክመኒስታን ሦስተኛ መሆናቸውን አስታወቀ።

ድርጅቱ አክሎ እነዚህ ሀገራት ውስጥ ሚድያዎች የመንግሥት አፈ-ቀላጤ ከመሆን ውጪ ሌላ ሥራ እንደማይሰሩ ገልፆ በኤርትራ ብቻ በቅርብ ዓመታት ሰባት ጋዜጠኞች የት እንደገቡ እንደማይታወቅ ይፋ አድርጓል።

ሉአላዊነቷን ከ27 ዓመታት በፊት ካወጀች አንስቶ በፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የምትመራው ኤርትራ ህገመንግስትም ሆነ ምርጫ ኖሯት አያውቀም። የአገሪቷም ፓርላማ ከተበተነ አስርት ዓመታት ያልፈዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 45 መስከረም 3 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here