አፋን ኦሮሞ እና ትግርኛ በጉግል መተርጎሚያ ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ

0
1464

ሐሙስ ግንቦት 4 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጉግል አፋን ኦሮሞ እና ትግርኛ ጨምሮ ከ300 ሚሊዮን በላይ በሆኑ ሰዎች የሚነገሩ 24 ቋንቋዎች በጉግል መተርጎሚያ ዝርዝሩ ውስጥ አካተተ፡፡

ኩባንያው በመተርጎሚያ ዝርዝሩ ባካተተው አዳዲስ ቋንቋዎች ውስጥ አስሩ በአፍሪካ የሚነገሩ ሲሆን አፋን ኦሮሞ ፣ ትግርኛ፣ ትዊ፣ ባምባራ፣ ክሪዎ፣ ሉጋንዳ ይገኙበታል፡፡

አፋን ኦሮሞ በኢትዮጵያ እና በኬንያ እንዲሁም ትግርኛ በትግራይና ኤርትራ በስፋት የሚነገሩ ቋንቋዎች ናቸው፡፡

አዲስ የተካተቱት ቋንቋዎች በጉግል ተርጓሚ የተካተቱ አጠቃላይ ቋንቋዎች ብዛት ወደ 133 ከፍ አድርጎታል፡፡

ኩባንያው አዲስ የተካተቱት ቋንቋዎች የቴክኖሎጂ ምዕራፍን እንደሚወክሉ ገልጾ፤ ምሳሌ ሳይኖር የሚተረጉም የማሽን መማሪያ ሞዴል እንደሚጠቀሙ አስታውቋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here