በአዲስ አበባ የ8ተኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 30 ይሰጣል ተባለ

0
2637

ሐሙስ ግንቦት 4 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከተማ አቀፍ የሆነው የ8ተኛ ክፍል (ሚኒስትሪ) ፈተናን ከ71 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ከሰኔ 27 እስከ ሰኔ 30 2014 ድረስ ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡

በአጠቃላይ 71 ሺህ 661 የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ለማስፈተን ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን በትምህርት ቢሮ ፈተና ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዲናኦል ጫላ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

የፈተና ዝግጅቱ ተጠናቆ የህትመት ሥራዉ የተዘጋጀ ሲሆን፤ በዕለቱ የማሰራጨት ሥራ ብቻ እንደሚቀርም ገልጸዋል፡፡

የፈተናዉን ምዝገባ በተመለከተ የተማሪዎች የአድሚሽ ካርድ በሚቀጥለው ሳምንት በየትምህርት ቤቶቹ እንደሚላክ እና ለተማሪዎቹም እንደሚተላለፍ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለስምንተኛ ክፍል ፈተና 211 የመፈተኛ ጣቢያዎች የተዘጋጁ ሲሆን፤ ጣቢያዎቹን ምቹ ናቸው የሚለውን ምልከታ እየተደረገ መሆኑን በማንሳት ቁጥሩ ከፍ አልያም ዝቅ ሊደረግ እንደሚችል ዳይሬክተሩ ለሬዲዮ ጣቢያው አብራርተዋል።

ፈተናው በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች እንደሚሰጥም ተገልጿል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here