መነሻ ገጽዜናየእለት ዜና”ሰላምንና አንድነትን ለማረጋገጥ ጉልበትን እንደ አማራጭ መውሰድ ሳይሆን በውይይት መፍታት ይገባል”:- ብፁዕ...

”ሰላምንና አንድነትን ለማረጋገጥ ጉልበትን እንደ አማራጭ መውሰድ ሳይሆን በውይይት መፍታት ይገባል”:- ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

ዕረቡ ግንቦት 10 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ሰላምንና አንድነትን ለማረጋገጥ ጉልበትን እንደ አማራጭ መውሰድ በማቆም የተከሰቱትን ችግሮች በውይይት ለመፍታት ኹሉም ኢትዮጵያውያን ጥረት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትረያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ገለጹ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የ2014ን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ በከፈቱበት ወቅት፤ ህዝቡን ወደ እርቅና ወደ ይቅርታ ማምጣት የሃይማኖት አባቶች ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

የእርቅን ጥቅም በመቀበል ወደ ተሻለ ነገር መራመድ ጊዜው የሚጠይቀው ተግባር ነው ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፤ ሰላም ለሃይማኖት መጠበቅና ለህዝብ ደኅንነት መረጋገጥ ትልቅ ዋጋ እንዳለውም ተናግረዋል።

ሰው ኹሉ ሰላምን ቢጠብቅ በኹሉ ነገር ስኬታማ መሆን እንደሚቻል የገለጹት ፓትረያርኩ፤ በአገሪቱ በተከሰቱ ግጭቶች ህዝቡ መንገላታቱን ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ የሚታየው ነገር ራስን የማስበለጥ እና የሌላውን የማሳነስ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህን ተግባር በማረም በመተሳሰብ፣ በትህትናና በፍቅር መመለስ እንደሚገባም ማስረዳታቸውን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል።

በተጨማሪም ቅዱስ ጉባዔው ራሱን ከማናቸውም አደረጃጀቶች ነጻ በማድረግ ለኹሉም ኢትዮጵያውያን ሠላም መሥራትና መጣር ይጠበቅበታል ሲሉ ብጹዕነታቸው አሳስበዋል፡፡

 

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች