መነሻ ገጽዜናወፍ በረር ዜናየፕላስቲክ ቆሻሻ እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል ኩባንያ ሊገባ ነው

የፕላስቲክ ቆሻሻ እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል ኩባንያ ሊገባ ነው

በዓመት 10 ሺሕ ቶን በላይ የፕላስቲክ ቆሻሻ እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል ኩባንያ በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለመግባት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።
ኩቢክ ኢትዮጵያ የተሰኘው መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው የፕላስቲክ አምራች የግል ኩባንያ፣ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በአጋርነት ለመሥራትና በአዳማ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ውስጥ የማምረቻ ሼድ በኪራይ ለመውሰድ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል ነው የተባለው።

ኢንቨስትመንቱ አካባቢን ከብክለት ነፃ ለማድረግ ትልቅ አስተዋፅኦ የሚያበረክት ነው የተባለ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቤቶችን ለመገንባት የያዘችውን እቅድ ለማሳካት ብሎም በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የግንባታ እቃዎች በመተካት ገበያውን የማረጋጋትና ምርትን የመጨመር አቅም የሚፈጥር መሆኑ ተጠቁሟል።

ኢንቨስትመንቱ በዓመት 125 ሺሕ ሜትሪክ ቶን የካርበን ልቀትን መቀነስ የሚያስችል ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ላለውም የግንባታና የሪል ስቴት ገበያ በተመጣጣኝ ዋጋ የግንባታ ቁሳቁሶችን ለማቅረብ ያስችላል ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪ ከ10 ሺሕ በላይ ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ የሥራ እድሎችን ለዜጎች የሚፈጥር ኩባንያ ነው ተብሎም ይገመታል።


ቅጽ 4 ቁጥር 185 ግንቦት 13 2014

ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች