መነሻ ገጽዜናወፍ በረር ዜና125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ

125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኤሌክትሪክ ባልደረሰባቸው ከተሞችና መንደሮች ፍትኃዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን እውን ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እያከናወኑ መሆኑን አስታወቀ።
ተቋሙ በ2014 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጿል።

ተቋሙ አገልግሎቱን ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ከ1997 ጀምሮ የአገር ዐቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም በመቅረፅ በርካታ ሥራዎች ሲያከናውን የቆየ ሲሆን፣ ፕሮግራሙ ከመጀመሩ በፊት 667 የገጠር ከተሞች ብቻ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ነበሩ።

ሆኖም ከ1998 ጀምሮ በተደረገው ከፍተኛ ፍትኃዊ የኤሌክትሪክ የማዳረስ ሥራ እስከ መጋቢት 30/2014 ድረስ 7 ሺህ 892 የገጠር ከተሞችንና መንደሮች ኤሌከትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ተመላክቷል።
ተቋሙ እንዲሁም በ2012 በጀት ዓመት 308፣ በ2013 በጀት ዓመት ደግሞ 341 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ነው የጠቆመው።

አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ሲታቃድ ዕድሉን የሚያገኙ አካባቢዎች ለይተው እንዲያሳወቁ የሚደረጉት ክልሎች መሆናቸውና እነሱ ቅድሚያ ይሰጣቸው ብለው ለይተው ሲያሳውቁ ሥራው እንደሚከናወን አገልግሎቱ አመላክቷል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን በብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም እ.ኤ.አ በ2025 ከዋናው ግሪድ 65 በመቶ እንዲሁም በአማራጭ የኃይል ምንጮች 35 በመቶ የሚሆነውን ኅብረተሰብ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ጥረት እያደረገ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል።


ቅጽ 4 ቁጥር 185 ግንቦት 13 2014

ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች