ብሪታኒያ ከኢትዮጵያ ጋር በአቪየሽን ዘርፍ በጋራ ለመስራት ፍላጎት አሳየች

0
610

ብሪታኒያ ከኢትዮጵያ ጋር በአቪየሽን ዘርፍ በጋራ ለመስራት ያላትን ፅኑ ፍላጎት በሚመለከት የብሪታኒያ የአፍሪካ ንግድ ኮሚሽነር ኢማ ዌድ ተናገሩ። ኮሚሽነሯ ዛሬ መስከረም 5/2012 የኢትዮጵያ አየር መንገድንና አቪየሽን ኢንዱስትሪውን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን አገራቸው ከአየር መንገዱ ጋር በተለያዩ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች አብራ ለመስራት ፍላጎት እንደላት አስታውቀዋል።

በዋናነትም በአየር መንገዱ ማስፋፊያ እና በአስተዳደራዊ ዘርፎች አብሮ የመስራት ፍላጎት እንዳላቸው አገራቸውን ፍላጎት አስታውቀዋል። ኢማ አያይዘውም ብሪታኒያ ከኢትዮጵያ ጋር በአቪየሽን ዘርፍ ጋር ባለፈ በግብርና  ማቀነባበሪያ እና በታዳሽ ኃይል ዘርፍም አብሮ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ተናግረዋል። የኹለቱን አገራት የረጅም ዘመን ግንኙነትና ብሪታኒያ የኢትዮጵያ የልማት አጋር እንደሆነችም አውስተዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here