ዳሰሳ ዘማለዳ ሰኞ መስከረም 5/2012

  • በ450 ሚሊዮን ዶላር ወጪ 2 መቶ ሚሊዮን ሰዎችን ማገልገል ይችላል የተባለ የካንሰር ሕክምና ሆስፒታል በኢትዮጵያ ሊገነባ ነው። ግንባታው የምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግስታት (ኢጋድ )ድጋፍ እንደሚገነባ እና የአባ አገራትን ዜጎች እንዲያገለግል የታሰበ ነው። (አዲስ ማለዳ )

……………………………………………..

2- ኢትዮጵያ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ በተመራው ልዑክ በመወከል በኦስትሪያ ቬይና በሚካሔደው በ63ኛው የዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኢነርጂ ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ትገኛለች። ሚንስትሩ ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክትር ኮርኔል ፌሩታ ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………..

3- የአማራ ክልል መንግስት ለስድስት የክልሉ አመራሮች ሹመት ሰጥቷል። በዚህም መሰረት የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት ግዛት አብዩ ጌታው የገጠር መሬት አስተዳድርና አጠቃቀም ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡

የጎንደር ከተማ ከንቲባ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት  ሙሉቀን አዳነ ጥሩነህ (ዶ/ር) ደግሞ የክልሉ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሆነው መሾማቸው ታውቋል፡፡

እንዲሁም  ብርሀኑ ጣዕም ያለው የክልሉ ንግድ ገበያ ልማት ቢሮ፣  ማማሩ አያሌው ሞገስ (ዶ/ር) የክልሉ የውሃ፣መስኖና ኢነርጅ ልማት ቢሮ፣  መለስ መኮንን ይመር (ዶ/ር) የግብርና ቢሮ ኃላፊ ሆነዋል ፡፡(አዲስ ማለዳ)

……………………………………………..

4-የጋምቤላ ሕዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋህአዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት በተለያዩ ድርጅታዊ አጃንዳዎች ዙሪያ ስብሰባ እያካሄደ ይገኛል።ማዕከላዊ ኮሚቴው ለ2 ቀናት በሚኖረው ቆይታ፤ የጋህአዴን የ2011 ዓ.ም የድርጅት ፖለቲካና የልማት ሥራዎች ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርበው ውይይት ይደረግበታል። የድርጅት ጽ/ቤቱ የ2012 ዓ.ም የውስጠ ድርጅት ሥራዎችና የጋህአዴን የአደረጃጀትና የአሠራር ሥነ-ምግባር ሠነድ ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግባቸውን ይጠበቃል።(ኤዜአ)

……………………………………………..

5- -የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ “ ጊፋታ አዋርድ” የተሰኘ የምስጋናና የእዉቅና ሽልማት ተበረከተላቸዉ፡፡

በወላይታ ሶዶ “አርአያዎቻችን በረከቶቻችን ናቸው” በሚል መሪ ሀሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ የምስጋናና እውቅና ስነ-ስርዓት ተካሂዷል፡፡

በስነ-ስርዓቱም አቶ ኃይለማርያምን ጨምሮ በተለዩ 5 ዘርፎች በአገርና በአለም አቀፍ ደረጃ በጎ ተጽዕኖ የፈጠሩ 45 ግለሰቦች የምስጋናና የእውቅና ሽልማትም ተበርክቶላቸዋል፡፡(ኤዜአ)

……………………………………………..

6- የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ እና ዘመናዊ የክፍያ ስርዓቱን ለቻይና እና መካከለኛው ምስራቅ ደንበኞቹ መዘርጋቱን አስታወቀ። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………..

7-አፍሮ ፅዮን ኮንስትራከሽን በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳድር ሰቆጣ ወረዳ 7 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጪ  ያስገነባውን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ አስመርቋል፡፡ትምህርት ቤቱን ያስመረቁት የአፍሮ ፅዮን ኮንስትራከሽን ባለቤት በጎ ፈቃደኛው  ሲሳይ ደስታ ናቸው፡፡ ትምህርት ቤቱ እያንዳንዳቸው አራት የመማሪያ ክፍሎች ያሏቸው ሁለት ሕንጻዎች እና የቤተ ሙከራ፣ መጸዳጃ ቤቶች እንዲሁም ሌሎችም የተለያዩ ክፍሎች እንዳሉ ታዉቋል።(አብመድ)
……………………………………………..

8-  ጣሊያን እና ሜክሲኮ በኢትዮጵያ ውስጥ በቱሪዝም ዘርፍ ያለውን ልማት ለመደገፍ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው አስታወቁ። (አዲስ ማለዳ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here