መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ከአብን ሥራ አስፈፃሚነታቸው መልቀቃቸውን በይፋ አሳወቁ

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ከአብን ሥራ አስፈፃሚነታቸው መልቀቃቸውን በይፋ አሳወቁ

ዕረቡ ግንቦት 17 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ትናንት ማምሻውን ባሰፈሩት መልዕክት አብን ባለፈው የካቲት አካሂዶት በነበረው ጊዜያዊ የአስፈፃሚ ሪፎርም ላይ ንቅናቄው በቀጣይ 3 ወር ውስጥ የሚያካሂደው ሪፎርም ተከናውኖ አዳዲስ አመራሮች እስኪመረጡ ድረስ ከ2 እስከ 3 ወር ላልበለጠ ጊዜ ወደ ሥራ አስፈፃሚ እንዲመለሱ የአብን ማዕከላዊ ኮሚቴ ወስኖ እንደነበር አስታውሰዋል።

አክለውም ”ወደ አመራርነት የመመለስ ፍላጎት ባይኖረኝም የድርጅቴ ውሳኔ ስለነበር ውሳኔውን ተቀብየው ቆይቻለሁ።” ብለዋል።

”ለአጭር ጊዜ ብየ የተመለስኩበት ጊዜ ስለተጠናቀቀ፣ እንዲሁም ወደፊት ጊዜው ሲደርስ በምገልፃቸው ምክንያቶች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ከአብን ሥራ አስፈፃሚ አባልነቴ በፈቃዴ የለቀቅሁ ሲሆን፤ በማኮ አባልነት ግን የአብን ሪፎርም በስኬት እስኪጠናቀቅ የምቀጥል ይሆናል።“ ሲሉም ገልፀዋል።

ዶ/ር ደሳለኝ “የንቅናቄው ሪፎርም በአጭር ጊዜ ተጠናቆ አብን ተጠናክሮ ሲቆም፤ ደግሞ ልክ ከአብን ሊቀ መንበርነቴ በገዛ ፈቃዴ እንደለቀቅሁት ኹሉ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነቴንም በገዛ ፈቃዴ በመልቀቅ አዳዲስ መሪዎች በማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ እድል እንዲያገኙ ለማድረግ መወሰኔን እገልፃለሁ።“ ያሉ ሲሆን ከአብን ሥራ አስፈፃሚነታቸው በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች