መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናከ250 በላይ የአገር ውስጥ እና የውጪ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት የንግድ ትርዒት እና ባዛር...

ከ250 በላይ የአገር ውስጥ እና የውጪ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት የንግድ ትርዒት እና ባዛር ሊከፈት ነው

ዕረቡ ግንቦት 17 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ከ250 በላይ ዓለማቀፍ የንግድ ተቋማት እና የአገር ውስጥ ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት ዓለማቀፍ የንግድ ትርኢት እና ባዛር ሊከፈት ነው፡፡

የኢትዮጵያ የንግድ እና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጁት 12ኛው የኢትዮ ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ግንቦት 25 ቀን 2014 በይፋ ይከፈታል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ተጠባባቂ ዋና ፀሐፊ ውቤ መንግስቱ እንደተናገሩት “የኢትዮጵያን ይግዙ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው የንግድ ትርኢት በአዲስ አበባ ኢግዚቢሽን እና ገበያ ልማት ማዕከል ለአምስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፤ ከዓለም ዓቀፍ የንግድ ተቋማት እና በአገር ውስጥ ኢንተርፕራይዞች ምርቶች እና አገልግሎቶች ይቀርባሉ፤ የአቻ ለአቻ የንግድ መድረክ ይካሄድበታል ፤ የፓናል ውይይቶች እንዲሁም ከ50 በላይ ከንቲባዎች የሚሳተፉበት የግሉ ዘርፍ እና ከንቲባዎች ምክክር መድረኮች የሚካሄዱበት ሲሆን፤ ሥራና ሠራተኞች የሚገናኙበት ትልቅ መድረክም ነው፡፡

ከመላው አገሪቱ የተወጣጡ ኢንተርፕራይዞች ተሳታፊ የሚሆኑበት ይህ ኤግዚቢሽን እና ባዛር፤ ከውጭ የሚመጡ የንግድ አካላት የሚሳተፉበት እንደመሆኑ ልምድ ለመለዋወጥ እና ትስስር ለመፍጠር ትልቅ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን የተናገሩት በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የገበያ ጥናት ዳይሬክተር ዘሪሁን አለማየሁ የንግድ ትርዒቱ የሥራ ዕድል በመፍጠር የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴርን ተልዕኮ ለማሳካት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ብለዋል፡፡

የኢትዮ ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ለተሳታፊዎች የገበያ ትስስር፣ የዕውቀትና ቴክኖሎጂ ጥምረት እና በአገር ውስጥ እና በውጪ አምራቾች አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች መካከል የልምድ ልውውጥ ማድረግን አልሞ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን፤ ከኮቪድ ሥርጭት በኋላ የመጀመሪያው መሆኑን ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ይህ ከ250 በላይ የአገር ውስጥ እና የውጪ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት የንግድ ትርዒት ሲከፈት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የንግዱ ማሕበረሰብ፣ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች