መነሻ ገጽሌሎችማኅበረሰብ አንቂ – የተከፈለበትየአቺባደም ስኬት :- ካንሠርን ተፋላሚው ቡድን

የአቺባደም ስኬት :- ካንሠርን ተፋላሚው ቡድን

በየአመቱ ከአለም ዙሪያ ከ 50,000 በላይ ሰዎች በቱርክ ወደሚገኙት አቺባደም ሆስፒታሎች ይጓዛሉ፡፡ ከእነዚህ ተጓዦች አብላጫዎቹ የካንሰር ታካሚዎች ናቸው፡፡ ተጓዦቹ በቴክኖሎጂ እና ልምድ ባካበተ የህክምና ቡድን የተዋቀረውን እንዲሁም ከዚህ ቀደም የተሳካ ህክምና ባገኙ ሌሎች ታካሚዎች የሚመሰገነውን አቺባደም ሆስፒታል ይመርጣሉ፡፡ በአቺባደም ኤምኤኤ ዩኒቨርሲቲ የሜዲካል ኦንኮሎጂ ዴፓርትመንትን የሚመሩት ዶክተር ኦዝለም ኤር አቺባደምበዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ታዋቂ የካንሰር ህክምና ማዕከሎች መካከል ጎልቶ እንዲታይ የሚያደርጉትን ሶስት ቁልፍ ነጥቦች ይገልጻሉ፡፡ እነዚህ ነጥቦች አጠቃላይ እንክብካቤ፣ ሁለገብ አቀራረብ እና በልክ የተመጠነ (ጠንቀኛዎቹን ህዋሳት ላይ አነጣጥሮ መፍትሄ የመስጠት) ህክምና ናቸው።

ለስኬታማ የካንሰር ሕክምና፣ የዘመኑን የተራቀቀ ማሽን ወይም ዝነኛ ሐኪም መያዝ ብቻ በቂ አይደለም። ይህ የግድ አስፈላጊ ቢሆንም ነገር ግን በቂ አይደለም፡፡ ለታካሚው እጅግ አስፈላጊው ነገር ትክክለኛውን ምርመራ ማድረግ እና ተገቢውን ህክምና በትክክለኛው ጊዜ መቀበል ነው፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ስራውን ጠንቅቀው በሚያውቁ እና በሺዎች ለሚቆጠሩ ጊዜያት ተግባራዊ ባደረጉት ሰዎች ድጋፍ ሲያገኙ ደህንነት ይሰማዎታል። ሂደቱ የታካሚውን ልዩ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ በተገቢው ቀዶ ጥገና፣ ኬሞ እና ራዲዮቴራፒ እያንዳንዳቸው በትክክለኛው ጊዜ እና ቅደም ተከተል ለመተግበር የሚያስችል ቡድን ይጠይቃል፡፡ አዳዲስ የሕክምና አማራጮችን ማግኘት፣ ስለ አመጋገብ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ ማህበራዊ እና ስነ ልቦናዊ ተግዳሮቶች በባለሙያ ምክር እየታገዙ ታካሚውን በእያንዳንዱ እርምጃ መደገፍ ያሻል፡፡ ይህም እምነትን የሚገነባ፣ መተማመንን የሚያጎለብት እና እድሎችን በሚሰጥ እውቀት እና ልምድን የሚፈልግ ነው።

በቱርክ ከሚገኙት ባለሞያዎቻችን ነጻ የህክምና ምክር ወይም አስተያየት ለማግኘት ያግኙን:-https://acibademinternational.com/

በልክ የተመጠነ ህክምና፡ጠንቀኛዎቹ ህዋሳት ላይ ማነጣጠር

ለካንሰር የግለሰብ ተኮር ህክምና ከምርመራ ይጀምራል፡፡ በመቀጠልም የህመሙን ደረጃ Grading እና Staging በፓቶሎጂ እና በምስል ምርመራዎች (ኤክስሬይ፣ አልትራ ሳውንድ . . . የመሳሰሉ) ይደረጋሉ፡፡ ፕሮፌሰር ኦዝለም ኤር እንደሚሉት Grading በተባለው የምርመራ ምዕራፍ የቱዩመር ሴሎቹ ሁኔታ ይጠናል፡፡ ከተለመዱት የአካላችን ህዋሶች ጋር ያላቸው ተመሳሳይነት እና ልዩነት ይታያል፡፡ Staging በተሰኘው የምርመራ ምዕራፍ ደግሞ እነዚህ ህዋሶች በሌላ የሰውነት ክፍሎችም ይገኙ እንደሆነ ይመረመራል፡፡ ለምሳሌ የጡት ካንሰር ህዋሶች ሳንባ እና ጉበትን ወደ መሳሰሉት በቅርብ ርቀት ወደሚገኙት የአካል ክፍሎች ተዛምቶ እንደሆነ የመለየት ስራ ይከናወናል፡ይህ ለግለሰቡ የተመጠነ ወይም የተበጀ ህክምና ይባላል፡፡

የካንሰር ሕክምና እንደ ታማሚው የተለየ የህመም ሁኔታ እና የዘረመል ባህሪያት ላይ ተመርኩዞ ግላዊ በሆነ መልኩ ሊተገበር ይችላል፡፡ ፕሮፌሰር ኦዝለም ኤር እንደሚናገሩት ዘመናዊ እና ልዩ መድሀኒቶች የካንሰር ህዋሶችን ለይተው ዒላማ በማድረግ ሊያጠቁ ይችላሉ። ይህም በተለምዶ ከካንሰር ጋር ጤናማ ህዋሶችንም ጨምሮ ሊጎዳ ከሚችለው ኬሞቴራፒ በተለየ መልኩ የታለመው ጠንቀኛ ህዋስ ላይ ማነጣጠር የሚያስችል ነው። ህክምናው በአብዛኛው በሳንባ ካንሰር፣ በጡት ካንሰር፣ በጨጓራና ትራክት እና በተወሰኑ ሌሎች የካንሰር ህመሞች ላይ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ “በአሁኑ ጊዜ በኦንኮሎጂ ትክክለኛውን ህክምና መስጠት ትልቁ የትኩረት ነጥብ ነው፡፡ ስለዚህም በተቻለ መጠን ካንሰርን ለይተን ለማከም ጥረት እናደርጋለን” ብለዋል የሕክምና ካንኮሎጂስቱ፡፡

ኢሚዩኖቴራፒ:- የሰውነትን ህመምን የመዋጋት አቅም መቀስቀስ

ኢሚዩኖቴራፒ በካንሰር ውስጥ ሕክምና አዲስ መስክ ነው፡፡ ይህም በሰውነት ውስጥ ያሉትን የበሽታ ተከላካይ ሕዋሳት የካንሰር ሕዋሳትን ቫይረሶችን እና ባክቴሪያዎችን እንዲያጠቁ የሚያስችል ነው። ፕሮፌሰር ኦዝለም ኤር እንዲህ ይላሉ፡፡ “የበሽታ ተከላካይ ሕዋሳት የእኛ ተዋጊዎች ናቸው፡፡ እነዚህ በሰውነታችን ውስጥ ያሉ ወታደሮች ሊባሉ የሚችሉ ሲሆን ለይተው የካንሠር ሴሎችን ማጥቃት ይችላሉ፡፡ ተዋጊዎቹ ህዋሳት በካንሰር ታማሚው አካል ውስጥ ብዙውን ጊዜ ተጎድተው የሚገኙ ቢሆንም በህክምና ለመቀስቀስ እንሞክራለን፡፡ ይህም በሽታ የመከላከል አቅማችንን ከፍ የሚያደርግ አማራጭ ነው።” ኢሚዩኖቴራፒ ከበርካታ አመታት በፊት በአደገኛ የቆዳ ካንሰር እና በሳንባ ካንሰር ላይ ጥቅም ላይ ይውል ነበር፡፡ “አሁን በሁሉም የካንሰር ዓይነቶች ሊተገበር ይችላል፡፡ ሆኖም አስቀድሞ የካንሰሩን አንዳንድ ባህሪያት መመርመር ያስፈልጋል፡፡ ይሄንን ተከትሎም ለእያንዳንዱ ታካሚ ግላዊ የሕክምና ሂደት እናቀዳለን” ብለዋል ፕሮፌሰሩ፡፡

ሰውነት በራሱ ካንሰርን እንዲፋለም ለማስቻል የሚሰጥ ህክምና የጎንዮሽ ጉዳቶች በአብዛኛው ከበሽታ መከላከል ጋር የተገናኙ እና ከልማዳዊው ኬሞቴራፒ የተለዩ ናቸው፡፡ ኤክስፐርቱ እንዲህ ሲል ያብራራል፡፡ “ለምሳሌ በህክምና ሂደቱ የፀጉር መርገፍ አይፈጠርም፡፡ ነገር ግን እንደ ሽፍታ ወይም ማሳከክ ያሉ ከሰውነት ቆዳ ጋር የተያያዙ የጎንዮሽ ውጤቶች እናያለን። ከጨጓራ ትራክት ሲስተም ጋር የተያያዙ አንዳንድ እንደተቅማጥ ያሉ ምልክቶች ልናይ እንችላለን፡፡ አለበለዚያም እንደ ታይሮይድ ወይም አድሬናል ችግሮች ያሉ አንዳንድ ሆርመሞን አመንጪ የኢንዶሮኒክ በሽታዎችን ሊስተዋሉ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ ሊታከሙ የሚችሉ ነገር ግን ጠቃሚ የጎንዮሽ ጉዳቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ ዶክተሩ እና የካንሰር ማእከሉ በዚህ ጉዳይ ላይ የካበተ ልምድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡

ሁለገብ አቀራረብ በሁለገብ የካንሰር ማዕከል

አጠራጣሪ የካንሰር ግኝቶች ካለዎት ዋና ሐኪምዎ ወደ ኦንኮሎጂስት እንደሚመራዎት ይጠበቃል፡፡ የኦንኮሎጂ በሽታዎችን መመርመር እና ማከም በባህሪዩ ውስብስብ ሂደት አለው፡፡ እናም የተለያየ እውቀት፣ ልምድ እና ቴክኖሎጂ ያስፈልገዋል፡፡ ካንሰር ያለበት ታካሚ የሕክምና ኦንኮሎጂስት፣ የጨረር ወይም የቀዶ ጥገና ኦንኮሎጂስት፣ ራዲዮሎጂስት ሊፈልግ ይችላል፡፡ “ከህክምና ኦንኮሎጂስት ጋር የሚሰሩ ሰራተኞች በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡ ነርስ, የአመጋገብ ባለሙያ፣ ማህበራዊ ሰራተኛ … እነዚህ ልዩ ባለሙያዎች በአንድ ማእከል ውስጥ የሚገኙ ከሆነ ትልቅ እድል ነው” ይላሉ ፕሮፌሰር ኦዝሌም ኤር፡፡ ጊዜ በካንሰር ህክምና ውስጥ ወሳኝ ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉም ባለሙያዎች ከጎንዎ ሆነው በቡድን የሚሰሩ ከሆነ፣ የህክምናው ሂደት ያለእንቅፋት እና ያለምንም መዘግየት በቅንጅት ይከናወናል።

የኦንኮሎጂ ማእከል አጠቃላይ የካንሰር ማዕከል መሆን አለበት፡፡  ‘አጠቃላይ’ ሲባል፣ ይህ ማዕከል የሜዲካል ኦንኮሎጂ፣ የጨረር ኦንኮሎጂ፣ የቀዶ ሕክምና ኦንኮሎጂ፣ ፓቶሎጂ፣ ሞለኪውላር ፓቶሎጂ፣ የኑክሌር ሕክምና እና የራዲዮሎጂ ክፍሎች ሊኖሩት ይገባል እንደማለት ነው። እነዚህ ክፍሎች በአንድ ማዕከል ውስጥ የሚገኙ ከሆነ እና ካንሰርን በመመርመር እና በማከም ረገድ ልምድ ያላቸው እንደሆነ የስኬቱ መጠን በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው» ሲሉ ፕሮፌሰር ኤር ያስረዳሉ። በአሲባደም ውስጥ እያንዳንዱ አዲስ ጉዳይ በልዩ ባለሙያተኞች የቲዩመር ቦርድ ውይይት ይደረግበታል፡፡ ሁለገብ በሆነ መንገድ የመድብለ ዲሲፕሊን አቀራረብ የሕክምና ዕቅዱ ተዘጋጅቶ በትክክል መፈጸሙን ያረጋግጣል፤ እንዲሁም ሁሉንም አማራጮች ግምት ውስጥ ያስገባል፡፡ ይህ እንደ አቺባደም ካለው አጠቃላይ የካንሰር ማዕከል ዋና ጥቅሞች አንዱ ነው፡፡ የካበተ ልምድ ከመያዙ ሌላ እና ማንኛውም የሚኖር አማራጭ ሁሉ እንደሚሞከር ማረጋገጫ ይሰጣል።

በተሻለ ሊታከም የሚችለው የካንሰር አይነት . . .

የካንሰር አይነት ምንም ይሁን ምን በመጀመሪያ ደረጃ ላይ የተገኘ ካንሰር ብዙውን ጊዜ ሊታከም ይችላል። ስለዚህ ዓመታዊ ምርመራዎችዎ እንዳያመልጥዎት እና ልዩ ትኩረት የሚሹ አንዳንድ አስቸኳይ ምልክቶችን ይመልከቱ። ፕሮፌሰር ዶ/ር ኦዝሌም ኤር “አንዳንድ ካንሰሮች በቤተሰብ ሊተላለፉ ይችላሉ፣ሌሎች ደግሞ እንዲሁ አልፎ አልፎ ሊከሰቱ ስለሚችሉ በማንኛውም ታካሚ ላይ የጤና እክል ሊያመጡ ይችላሉ። በቤተሰባችን ውስጥ የካንሰር በሽታ ካለ የካንሰሮች አዝማሚያ አለመኖሩን ማረጋገጥ አለብን፡፡ ለምሳሌ በእህታችን፣ በአክስታችን ወይም በእናታችን ላይ የጡት ካንሰር ወይም በቤተሰብ ውስጥ አንድ አይነት ካንሰር ቢከሰት ሁኔታውን በተለየ መመልከት ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ በቤተሰባችን ውስጥ በወጣት ላይ ማለትም እድሜው ከ50 ዓመት በታች የሆነ ሰው ላይ ካንሰር ከተከሰተ ጥንቃቄ ማድረግ እና ወደ አጠቃላይ ሀኪሞቻችን ሄደን የዘረመል ምክክር ማድረግ አለብን።”

በቱርክ ከሚገኙት ባለሞያዎቻችን ነጻ የህክምና ምክር ወይም አስተያየት ለማግኘት ያግኙን:- https://acibademinternational.com

ተመሳሳይ ጽሁፎች 


- ይከተሉን -Social Media

ለስኬታማ የመካንነት ህክምና ጠቃሚ 3 ቁልፍ ነገሮች – AM (addismaleda.com)

አቺባደም ሄልዝ ኬር ግሩፕ በኢትዮጵያ ጽ/ቤቱን ከፈተ – የተከፈለበት – Addis Maleda

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች