ድምጻዊ አብርሀም በላይነህ ( ሻላዬ) በተጠረጠረበት የግድያ ወንጀል ለ2ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረበ

0
1923

አርብ ግንቦት 19 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ድምጻዊ አብርሀም በላይነህ በግድያ ወንጀል መጠርጠሩን ተከትሎ ለኹለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርቧል።

መርማሪ ፖሊስም ከዚህ በፊት በተሰጠው የ14 ቀን የሰራውን የምርመራ ሥራ ሪፖርት ለፍርድ ቤቱ ያቀረበ ሲሆን፤ በዚህም የሟች አስከሬን ምርመራ ለማከናወን ለህክምና ተቋም ደብዳቤ መላኩን የህክምና ማስረጃ እየተጠባበቀ መሆኑን ለችሎቱ አስረድቷል።

ድምጻዊ አብርሀም ከሟች ጋር ያደረገውን የስልክ ለማጣራት ለኢትዮ ቴሌኮም ደብዳቤ መላኩንና ተጨማሪ ምርመራ ለማከናወን ተጨማሪ የ14 ቀን ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።

ድምጻዊ አብርሀም በላይነህ በበኩሉ ከዚህ በፊት 14 ቀን የተሰጠ በመሆኑ አሁንም 14 ቀን ሊሰጥ እንደማይገባ በመግለጽ፤ ምርመራቸውን ለመጨረስ አጭር ቀጠሮ ይሰጣቸው ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎትም ፖሊስ የጀመረውን የምርመራ ውጤት ለመጠባበቅ ተጨማሪ 12 ቀን በመፍቀድ ለሰኔ 1ቀን 2014 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ዘግባለች።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here