የተፈጥሮ ጋዝና የማዕድን ፈቃድ ወስደው ውጤት ላላሳዩ ኩባንያዎች ማስጠንቀቂያ ተሰጠ

0
1245

በነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ እንዲሁም ወርቅ ምርት እና ፍለጋ ላይ ተሰማርተው ለረጅም ዓመታት ውጤት ላላሳዩ ኩባንያዎች ማስጠንቀቂያ መስጠቱን የማዕድን ሚኒስቴር ገለፀ።
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለኢፌዴሪ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባ የ2014 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት እንደገለጸው፣ በነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ እንዲሁም ወርቅ ምርት እና ፍለጋ ላይ ተሰማርተው ለረጅም ዓመታት ውጤት ላላሳዩ ኹለት ኩባንያዎች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል ብሏል።
የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥተዋል ከተባሉ ኩባንያዎች ውስጥ አንዱ ጆሊ ጂሲኤል የተባለው በአራት የማዕድን ፍለጋ እና አንድ የማዕድን ልማትና ምርት ፈቃድ የወሰደ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ ኩባንያው ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት የሚጠበቅበትን ሥራ ያላከናወነ መሆኑን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በግምገማ ማረጋገጡን አሳውቋል።
ኩባንያው ያለበትን የፋይናንስና የቴክኒክ አቅም ውስንነት እስከ በጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ ድረስ ካላሟላ ስምምነቱ የሚቋረጥ ስለመሆኑ የመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል ነው የተባለው።
በተጨማሪም ኬፊ ሚኒራልስ (ቱሉ ካፒ) ኩባንያን በሚመለከት የወርቅ ምርት ፈቃድ ከወሰደበት እ.ኤ.አ 2015 ጀምሮ ባለፉት ስምንት ዓመታት ውል በገባው መሠረት የምርት ሥራ አለማከናወኑን ሚኒስትሩ ገልጿል።


ቅጽ 4 ቁጥር 186 ግንቦት 20 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here