ዳሰሳ ዘማለዳ ዓርብ መስከረም 9/2012

0
704
  • ዩኒቨርስቲዎች የ2012 አዲስ የተመደቡ መደበኛ ተማሪዎችን ከመስከረም 25 እስከ 29/2012 ድረስ መቀበል እንደሚጀምሩ የከፍተኛ ትምህርት ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………….

  • በሕገ ወጥ መንገድ ለገበያ ሊቀርብ የነበረ 52 አይሱዙ ሙሉ እህልና ጥራጥሬ ዛሬ ዓርብ መስከረም 9/2012 በአዲስ ከተማ ክፍል ከተማ ልዩ ስሙ ኳስ ሜዳ በተባለ ቦታ በአዲስ አበባ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሏል። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………….

  • የዓለም የሰላም ቀን ነገ ቅዳሜ መስከረም 10/2012 በዓለም አቀፍ ደረጃ ይከበራል። የዘንድሮው የሰላም ቀንም ‹‹የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል ለሰላም ›› በሚል መሪ ቃል ይከበራል። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………………

  • መስከረም 3/2012 በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ መሐሙድ ሙዚቃ ቤት አካባቢ በሚካኤል ገብሩ ላይ ግድያ ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ኹለት ግለሰቦች ተይዘው ምርመራ እየተካሔደባቸው የሚገኝ ሲሆን ተጨማሪ አንድ ተጠርጣሪም ክትትል እየተደረገበት እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። (አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………………

  • የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በ20 ሚሊዮን ብር የዓሳ ጫጩት ማስፈልፈያ ማዕከል እያስገነባ እንደሆነ አስታወቀ። (አብመድ)

………………………………………………………….

  • ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለመጠቀም የሚያስችላትን ተቸማሪ ስምምንት ፕሮቶኮል ፈርማለች። ኒውክሌርን ለማንኛውም ሰላማዊ ዓላማ መጠቀም የሚያስችላት ስምምነት እንደሆነም ታውቋል። (አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ)

……………………………………………………………..

  • በአዲስ አበባ ከተማ በዋጋ ማናር ምክንያት የተጠረጠሩ 609 ድርጅቶችና የንግድ ሱቆች መታሸጋቸውን የአዲ አበባ መስተዳደር ንግድ ቢሮ ይፋ አድርጓል። (ኢዜአ)

……………………………………………………………………..

  • በ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ወጪ የሚገነባው እና 380 ሜትር ርዝመትና 43 ሜትር ስፋት ያለው የባህር ዳር አባይ ወንዝ ተለዋጭ ድልድይ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተጣለ። (ዋልታ)

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here