በ2011 በጀት ዓመት 138 ሚሊዮን ብር ወደ መንግስት ካዝና ተመልሷል።

0
761

መንግስት በ2011 በጀት ዓመት ከሙስና ጋር በተያያዙ ወንጀሎች የሀብት ማስመለስ ስራዎችን በመስራቱ 138 ሚሊዮን ብር ወደ መንግስት ካዝና መመለስ እንደተቻለ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል። በሙስናና እና ብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ መንግስት ከፍተኛ ስራ ስራዎች መስቱን እና ወንጀለኛ ሆነው በተገኙ ግለሰቦች ላይም ክስ እንዲመሰረት እንደተደረገ በፌደራል ዐቃቤ ሕግ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር   ተረፈ አሰፋ አስታውቀዋል።

ዳይሬክቶሬቱ የወንጀሉን ዉስብስብት በመረዳትና ትኩረት ሰጥቶ ለመሰራት ያመቺ ዘንድ በሙስና ወንጀል የተገኙትን ሀብቶች የሚያስመልስና የሚያስወርስ እንዲሁም በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊና በፍትህ አስተዳደር ዘርፍ የሚሰሩ ማስተባበሪያዎችን በማደራጀት በበጀት ዓመቱ በሙስና ወንጀሎች ዙሪያ ስኬታማ ተግባራትን ለማከናወን የሚያስችል አደረጃጀት መፍጠር መቻሉን  ተረፈ አክለዉ ገልፀዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here