ኢትዮጵያ ባለፉት ኹለት ወራት ወደ ውጭ ከተላከ የቡና ንግድ 183 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቷን ንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሐምሌና ነሐሴ 2011 ከ52 ሺሕ 300 ቶን በላይ ቡና ወደ ውጭ አገራት የተላከ ሲሆን፣ ከባለፈው 2010 ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር ከ6 ሺሕ 585 ቶን በላይ ጭማሬ ማሳየቱንም ለማወቅ ተችሏል። ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ6 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ጭማሬ አሳይቷል።
ቡና ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ቀዳሚ ሲሆን፣ በባለፈው በጀት ዓመት ብቻ ከ774 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለአገሪቷ አስገኝቷል።
በአገሪቱ ከ442 በላይ የቡና ላኪዎች ሲኖሩ፣ በሥራ ላይ ያሉት ከ290 የንግድ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። በተመሳሳይ ከ5 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ገበሬዎች ቡና የሚያመርቱ ሲሆን፣ ከገቢም አንጻር ቡና ቀዳሚ ቢሆንም፣ በቅርቡ በታየው ዓለም ዓቀፍ የዋጋ መቀነስ ጋር ተያይዞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መቀዛቀዝ አጋጥሞ ነበር።
በባለፈው ዓመት በ13 ዓመታት ውስጥ ዝቅተኛው ዓለም ዓቀፍ የቡና ዋጋ ተመዝግቦ የነበረ ሲሆን 0.87 ፓውንድ ደርሶ ነበር። ይህ ከዛሬ ስምንት ዓመት በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በሦስት እጥፍ ያነሰ ነው። የዋጋ ማሽቆልቆሉ ቢቀጥልም በዚህ ዓመት የአገሪቱ የቡና ምርት 7 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።
ቅጽ 1 ቁጥር 46 መስከረም 10 2012



