በወለጋ ዞን በአንድ ሳምንት ሶስት የቦምብ ጥቃቶች ተፈጸሙ

0
850

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን መነስቡ ወረዳ መንዲ ከተማ፣ በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ከተማ ቅዳሜ መስከረም 3/2011 ሌሊት፣ እሁድና ማክሰኞ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት አምስት ሰው ሲገደል፣ ሶስት ሰዎች መቁሰላቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናገሩ።

የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳደር የጸጥታ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አብዩ ምኅረቱ፣ ጥቃቱን የፈጸሙት የኢትዮጵያ መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ያልተቀበሉ የሸኔ ታጣቂ ቡድን አባላት ናቸው ሲሉ ገልጸዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው ከዚህ ቀደም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አባል በነበሩ ሰዎች ላይ ነው። “ለምን እጃችሁን ሰጣችሁ?” በሚል በተቀመጡበት የቦምብ ጥቃት በመፈጸም ሶስት ሰዎች መቁሰላቸውንና አንድ ሰው መሞቱን ተናግረዋል።

በቄለም ወለጋ፣ ጉዳሚ ወረዳ ባለፈዉ ቅዳሜ ማታ በተነሳ ግጭት ሁለት የከተማይቱ ነዋሪዎች ሲገደሉ፣ በማግስቱ እሁድ በምዕራብ ወለጋ የጉልሶ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አበበ ተካልኝ ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸውን ያስታወቁት ኃላፊው፣ ማክሰኞ በቄለምና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ሶስት ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 46 መስከረም 10 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here