መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናየኢትዮጵያ ባንኮች ላይ ባነጣጠረ የማጭበርበር ወንጀል ከ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ባላይ...

የኢትዮጵያ ባንኮች ላይ ባነጣጠረ የማጭበርበር ወንጀል ከ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ባላይ መመዝበሩ ተገለጸ

ሰኞ ግንቦት 22 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮችን ባነጣጠረ የማጭበርበር ወንጀል ከ1 ቢሊየን 896 ሚሊየን ብር በላይ መመዝበሩን በፍትህ ሚኒስቴር የተደረገ ጥናት አመላከተ።

ከ2009 ጀምሮ በተካሄደው በዚህ ጥናት ከ370 ቢሊየን ብር በላይ በባንኮች ላይ ማጭበርበር ተሞክሮ እንደነበር ተመላክቷል።

ጥናቱን ተከትሎ የፍትህ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ እና የተለያዩ ባንኮች ፕሬዚዳንቶች፣ የኢትዮ ቴሌኮምና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ነው።

ጥናቱ በባንኮች ላይ የሚፈጸሙ የማጭበርበር ወንጀሎች መንስኤዎቻቸው እና የአፈጻጸም ዘዴያቸውን በመለየት የመፍትሔ ሃሳቦችን ለማቅረብ በፍትህ ሚኒስቴር የተደረገ መሆኑ ተገልጿል ሲል ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡

በውይይቱም በኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮችን ባነጣጠረ የማጭበርበር ወንጀል ከ1 ቢሊየን 896 ሚሊየን ብር በላይ መመዝበሩን የተደረገው ጥናት መመላከቱም ተገልጿል።

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች