“በተወሰደዉ ጠንካራ እርምጃም በታጣቂ ቡድኑ ላይ ከፍተኛ ሰበአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሷል” የጋንቤላ ክልል መንግስት

0
1370

ማክሰኞ ሰኔ 7 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በጋምቤላ ከተማ ተኩስ ከፍተው በነበሩ የሸኔና የጋምቤላ ነፃነት ግንባር ላይ በፀጥታ አካላት በተወሰደ ጠንካራ እርምጃ ከተማዉን ማረጋጋት መቻሉን የክልሉ መንግስት አስታወቀ።

በዚህም በተወሰደዉ ጠንካራ እርምጃም በታጣቂ ቡድኑ ላይ ከፍተኛ ሰበአዊና ቁሳዊ ኪሳራ መድረሱ ነው የተገለፀው።

በከተማው ከጠዋቱ 12:30 ጀምሮ ያለማቋረጥ ለረጅም ሰዓት የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ እንደነበር አስታውሶ፤ በአሁኑ ሰዓት ተቆርጠው የቀሩ የቡድኑ አካላትን የማጥራት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አስረድቷል።

ታጣቂ ቡድኑን ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ በመንግስት ፀጥታ አካላት እየተወሰደ ያለዉ የማያዳግም እርምጃም ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል።

የክልሉ መንግስት፤ የከተማው ህብረተሰብ ከቤት ባለመውጣት የፀጥታ ሀይሉ እያደረገ ላለው የህግ ማስከበር ተግባር ተባባሪ በመሆኑ ምስጋና አቅርቧል።

የደረሰው ጉዳት በቀጣይ እንደሚገለጽ የጠቆመው የክልሉ መንግስት ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጎን በመሆን የተለመደ ትብብሩን እንዲያጠናክር ጠይቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here