ዳሰሳ ዘማለዳ ሰኞ መስከረም 12/2012

0
548
  • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) የሔሰን የሰላም ሽልማት ዛሬ ሰኞ መስከረም 12/2012 በጀርመን አገር የተበረከተላቸው ሲሆን ጠቅላይ ሚንስትሩን ወክለው የኢፌዲሪ የሰላም ሚንስትር ሙፈሪሐት ካሚል ሽማቱን ተቀብለዋል። (አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………………….

  • የኢፌዲሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከአሜሪካው የልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤድ) እና ከሕፃናት አድን ድርጅት (ሴቭ ዘ ችልድረን) ጋር ለተማሪዎች ክህሎት ማሳደጊያ በሚል የኹለት ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ። ድጋፉ ባህር ዳር፣ ሐዋሳ፣ ጅማ፣ ጅግጅጋ፣መቀሌ ዩኒቨርስቲዎችን የሚደርስ ይሆናል። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………………….

  • ኢትዮጵያ ንግድ መረከብ ባለፈው ዓመት 2011 በጀት ዓመት 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ማትረፉን አስታወቀ። ድርጅቱ በበጀት ዓመቱ 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን ጭነት ያጓጓዘ ሲሆን፤ ከዚህም ውስጥ 2 ሚሊዮን ቶን የሚሆነው ማዳበሪያ እና ስንዴ እንደሆነም ታውቋል። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………………..

  • ዛሬ መስከረም 12/2012 በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ቡልጋሪያ በተባለ ስፍራ ኹለት ሰዎች ይዘውት ሲንቀሳቀሱ የነበረው ብረት ከኤሌክትሪክ ገመድ ጋር በመነካካቱ ህይወታቸው አለፈ። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………….

  • ኢትዮ ቴሌኮም የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን ከዚህ ቀደም ይፋ አድርጓቸው ከነበረው የክፍያ ቦታዎች በተጨማሪ እና ለድኅረ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የአገልግሎት ክፍያቸውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መክፈል እንዲችሉ በማሰብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ስምምነት ተፈራረመ። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………………….

  • -እስራኤል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ(ዶ/ር) ጉብኝት ወቅት ለመደገፍ ቃል የገባቻቸው ፕሮጀክቶች ወደ ተግባር ሊገቡ እንደሆነ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ራፋኤል ሞራቭ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴኤታ ጀማል በከር ጋር በተወያዩበት ጊዜ ተናግሯል። በቴክሎጂ የተደገፈ የዓሳ ሃብት ልማት፤ የበረሃማ ቦታዎች ልማት፤ የበይነ መረብ ደኅንነትና ለቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ምቹ ከባቢያዊ ሁኔታን ለመፍጠር ቃል ተገብቷል።(አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………………………

  • መንግስት በ3 ነጥብ 4  ቢሊየን ብር በሚገመት ወጪ አራት ሚሊየን ኩንታል ስንዴ ሊገዛ ነዉ።የተገዛዉ ስንዴ ገብያዉን ለማረጋጋት የሚዉል ሲሆን 1650 ዳቦ ቤቶች እና 44 ዱቄት ፋብሪካዎች ይከፋፈላል።(አዲስ ፎርቹን)

………………………………………………………………….

  • – ኦዳ የተቀናጀ የትራንስፖርት አገልግሎት በ400 ሚሊየን ብር ከውጭ አገር ያስገባቸውን  ለትራንስፖርት አገልግሎት የሚዉሉ 50 አውቶብሶችን እና በ42 ሚሊየን ብር የተገነቡ ኹለት የነዳጅ ማደያዎችን እሁድ መስከረም 11/2012 በይፋ ስራ አስጀምሯል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here