ቦይንግ ኩባንያ 144 ሽሕ 500 ዶላር ካሳ በነብስ ወከፍ ሊከፍል ነው

0
730

የአሜሪካው አውሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ ባሳለፍነው ዓመት ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው ቦይንግ 737 ማክስ 8 ከአዲስ አበባ ናይሮቢ በጉዞ ላይ ባጋጠመው አደጋ 157 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን ተከትሎ ለተጎጂ ቤተሰቦች በነብስ ወከፍ 144ሽሕ 500 ዶላር ካሳ ሊከፍል እንደሆነ ይፋ ሆኗል።

ኩባንያው ባሳለፍነው ዓመት ሰኔ ወር ላይ ለመክፈል ከተስማማው 100 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ የሚሰጥ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ግማሹ ደግሞ አደጋው በደረሰበት አካባቢ ለሚገኘው ማኅበረሰብ የትምህርት ቤትና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ማስገንቢያ የሚውል እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል። በአደጋው 35 የተለያዩ አገራት ዜጎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን የሚከፈለው ካሳ በበቂ ሁኔታ የሚክስ አይደለም የሚሉ ወገኖችም ከወደ አሜሪካ እየተሰማ ነው።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here