የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ጴጦሮስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ አድርጎ መረጠ

0
1448

ዕረቡ ግንቦት 24 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦት 2014 ርክበ ካህናት እያከናወነ የሚገኘው ጉባኤ የቀጠለ ሲሆን፤ ጉባኤው ዛሬ ባካሄደው ምርጫ የባሕርዳር እና አካባቢው አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ እንዲሁም የኒዮርክ እና አካባቢው አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በማድረግ መርጧል።

ጉባኤው በዛሬው ዕለት ግንቦት 24 ቀን 2014 በተካሄደው ምርጫ አርባ አምስት ሊቃነ ጳጳሳት የተገኙ ሲሆን፤ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅነት ከተወዳደሩት ውሰጥ ብፁዕ አቡነ አብርሃም 26 ድምጽ በማግኘት ሲመረጡ፤ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ 20 ድምጽ በማግኘት መመረጣቸውን ከኢኦተቤ ቴቪ ( EOTC TV) ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here