በጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የተመራ ከፍተኛ የልዑክ ቡድን ባሌ ሮቤ ገባ

0
950

ሐሙስ ግንቦት 25 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በጠቅላይ ሚኒስትር (ዶ/ር) ዐቢይ አህመድ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ለሥራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት ባሌ ሮቤ ገብቷል።

በጉብኝቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተጨማሪ የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ ኡስማን ዲዮን እንዲሁም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተሳታፊ መሆናቸውን ኢብኮ ዘግቧል።

የልዑካን ቡድኑ በባሌ ዞን እየተከናወኑ ያሉ የግብርና ሥራዎችን ተዘዋውሮ ይመለከታል ተብሎ ይጠበቃል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here