በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ ለህወሃት ከ800 ሺህ ብር በላይ ሊያስተላልፉ የሞከሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

0
971

ሐሙስ ግንቦት 25 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ በሽብርተኝነት ለተፈረጀው የህወሃት ቡድን ከ800 ሺህ ብር በላይ ሊያስተላልፉ የሞከሩ ተጠርጣሪዎች በፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለፀ።

በላስታ ወረዳ ከላልይበላ ከተማ ወደ ጥላት አካባቢ ጨለማን ተገን በማድረግ ሲሄድ በላስታ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ከሌሊቱ 6፡ 00 እስከ 11፡00 ስዓት በተደረገ ስምሪት 594 ሺህ 260 ብር / አምስት መቶ ዘጠና አራት ሺህ ኹለት መቶ ስልሳ ብር/ በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ሥር መዋሉን የላስታ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ተገኘ ወርቁ ገልፀዋል፡፡

እንደ ኃላፊው ገለፃ፤ በትናንትናው ዕለት በተሰጠው ፖሊሳዊ ትዕዛዝ ለ14 ፖሊስና ሚሊሻ የፀጥታ አካላትን ስምሪት በመስጠት ሌሊት የሚንቀሳቀሱ ባጃጅና ቲዎታ መኪናዎች ላይ በተደረገው ፍተሻ፤ አንድ ባጃጅ ውስጥ 396 ሺህ 900 ብር / ሦስት መቶ ዘጠና ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር/ ባለቤት የሌለው እና 197 ሺህ 360 ብር / አንድ መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ስልሳ ብር/ በተለያዩ ሰዎች ኪስ እና 50 ፍሬ ሳሙና በዛሬው ዕለት ከ11 ሰዎች ጋር በጥርር በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡

ከድንበር አካባቢ ለጥላት ሊሻገር የነበረ 210 ሺህ ብር /ሁለት መቶ አስር ሺህ ብር/ ከቀናት በፊት መያዙን ጠቅሰው በዚህ ሳምንት እንደ ወረዳ 804 ሺህ 260 ብር /ስምንት መቶ አራት ሽህ ኹለት መቶ ስልሳ ብር / በቁጥጥር ሥር መዋሉን ገልፀዋል፡፡

ኃላፊው አያይዘውም ማህበረሰቡና የፀጥታ አካላት ህገወጥ ዝውውርን ቁጥጥር ለማድረግ እየሰሩ ያሉትን አካላት አመስግነው በቀጣይም ህብረተሰቡ ማንኛውንም ጥረጣሪ ሲመለከት ለፖሊስ ጥቆማ የመስጠት ባህሉን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ማሳሰባቸውን ከላስታ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here