የሜቴክ የቀድሞ 4 አመራሮች ከተከሱሰበት የሙስና ወንጀል ክስ ከእስር እንዲፈቱ ታዘዘ

0
837

ሐሙስ ግንቦት 25 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የቀድሞ የብረታብረትና ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ)4 አመራሮች ከተከሱሰበት የሙስና ወንጀል ክስ ከእስር እንዲፈቱ ታዘዘ።

አራቱ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ከተወሰነባቸው የእስራት ቅጣት በላይ በእስር በመቆየታቸውና የእስር ጊዜያቸውን በማጠናቀቃቸው ነው እንዲፈቱ የታዘዘው።

የቀድሞ የብረታብረትና ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን ሀላፊዎች ሌ/ኮ ሰጠኝ ካሳይ፣ ኮነሬል ፍጹም አብርሃ፣ ሻለቃ ዋልታንጉስ ተስፋው እና ሻለቃ ክንድያ ግርማይ ሲሆኑ፤ የኃይል ትራንስፎርመር እና ባለ 3 ፌዝ ተርሚናል ኮኔክተር ለኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ለማቅረብ የተገባ ውል ላይ ያለጨረታ ግዢ ፈጽመዋል ተብለው በዓቃቢህግ በቀረበባቸው የሙስና ክስ በወንጀል ህግ 32 /1 ሀ እና የሙስና ወንጀል አዋጅ. ቁ 881/2007 አንቀጽ 91 ሀና ለ ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት በየደረጃው እንዲከላከሉ ብይን መሰጠቱ ይታወሳል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ተከሳሾቹ ያቀረቡትን የመከላከያ ማስረጃ ከመረመረ በኋላ በዓቃቢህግ ያቀረበውን ማስረጃ በተገቢው አልተከላከላችሁም ሲል የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎባቸው ነበር።

ተከሳሾቹ የቀረቡትን የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን ለአገር ያበረከቱት ሙያዊ አስተዋጾ እና የበጎ አድራጎት ሥራ በቅጣት ማቅለያ አስተያየት ተይዞላቸዋል።

በዚህም ፍርድ ቤቱ ሻለቃ ክንድያ ግርማይን 2 ዓመት ከ9 ወር እስራትና 400 ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ የወሰነ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ ሦስት ተከሳሾች ደግሞ በ3 ዓመት እስራትና 500 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።

ይሁንና ተከሳሾቹ ከተወሰነባቸው የእስራት ጊዜ በላይ ከጥቅምት 30 ቀን 2011 ጀምሮ በእስር በማሳለፋቸውና የእስር ጊዜያቸውን በማጠናቀቃቸው ከእስር እንዲፈቱ መታዘዙን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ከችሎት ዘግባለች።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here