ባለፉት 10 ቀናት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ታካሚዎች ለኮቪድ 19 ህክምና ወደ ሆስፒታል እየገቡ ነውም ተብሏል
ሰኞ ግንቦት 29 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በአገራችን ከ40 ቀናት እረፍት በኋላ በኮቪድ19 ምክንያት አንድ ሞት መስተናገዱን የኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ያሬድ አግደው አስታወቁ።
ዶክተር ያሬድ አግደው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለፁት፤ባለፉት አስር ቀናት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ታካሚዎች ለኮቪድ 19 ህክምና ወደ ሆስፒታል እየገቡ ይገኛሉ።
በዚህም ምክንያት የአንድ ሰው ሞት መስተናገዱን የገለፁት ዶክተር ያሬድ፤ ሌላ የኮቪድ19 ማዕበል በአገራችን በድጋሚ እንዳይከሰት አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ሀላፊነታችንን እንወጣ ሲሉ በመልዕክታቸው አሳስበዋል።




