መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናበመዲናዋ ትናንት ማምሻውን በጣለው ዝናብ 7 ቤቶች ከፍተኛ አደጋ ደረሰባቸው

በመዲናዋ ትናንት ማምሻውን በጣለው ዝናብ 7 ቤቶች ከፍተኛ አደጋ ደረሰባቸው

ሰኞ ግንቦት 29 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ትናንት ማምሻውን በጣለው ዝናብ 7 ቤቶች ከፍተኛ አደጋ እንደደረሰባቸው የእሳት እና የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ከሰሞኑ ቀለል ያሉ የጎርፍ አደጋዎች እየደረሱ እንደሚገኙ የተገለፀ ሲሆን፤ በሶስት አካባቢዎች ድንገተኛ አደጋዎች ደርሰዋል፡፡

የጎርፍ አደጋዎቹ የደረሱት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት በተለምዶ የሺ ደበሌ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር፣ አንድ ባጃጅ ተሽከርካሪ ላይ የደረሰ የእሳት አደጋ ሲሆን፣ በአደጋው ምክንያት 40 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ውድመት ደርሶበታል ተብሏል፡፡

ሌላኛው አደጋ የደረሰው እዛው ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ላይ አየር ጤና አካባቢ በመኖርያ ቤቶች ላይ የደረሰ የጎርፍ አደጋ ነው፡፡

ሦስተኛ የጎርፍ አደጋ የደረሰው በኮሌፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሦስት በተለምዶ ስልጤ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ላይ ነው፡፡

በእነዚህ አደጋዎች ምክንያትም ግምቱ 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ለውድመት መዳረጉን፣ የእሳት እና የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ስምንት ሚሊዮን ብር የሚሆን ንብርት ደግሞ ከጉዳት ማዳን መቻሉን ንጋቱ ለሬዲዮ ጣቢያው ተናግረዋል፡፡

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች