የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የሞጆ ደረቅ ወደብ የማስፋፊያ ፕሮጀክትን ጎበኙ

0
976

ማክሰኞ ግንቦት 30 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ መንግስት እና በዓለም ባንክ ትብብር እየተገነባ የሚገኘው የሞጆ ደረቅ ወደብ የማስፋፊያ ፕሮጀክት የሲቪል ምህንድስና ሥራውን ጎብኝተዋል፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ እና ሚኒስትር ዴኤታ ደንጌ ቦሩ እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የማስፋፊያ ግንባታው የሥራ ሂደት የተጎበኘው፡፡

በቻይናው ተቋራጭ ሲሲኢሲሲ እየተገነባ የሚገኘውን የሞጆ ደረቅ ወደብ የግንባታ ሂደትን በተመለከተ የፕሮጀክቱ ማናጀር ኢ/ር ደሣለኝ ጌታሁን አማካኝነት አሁናዊ ገፅታው ላይ ገለፃ ተደርጓል፡፡ የሲቪል ምህንድስና ሥራው በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስም፤ ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያን የወጪና ገቢ ንግድ በማሣለጥ ወደ ላቀ የእድገት ጎዳና የሚያሸጋግር ግዙፍ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ነው በማለት፤ የኢትዮ ጅቡቲን የኢኮኖሚ ትስስርም ይበልጥ የሚያጠናክር በመሆኑ መንግስት በከፍተኛ ክትትልና ቁርጠኝነት ፕሮጀክቱን ከግብ ለማድረስ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡

የሞጆ ደረቅ ወደብ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ስድስት የማቀዝቀዣ መጋዘኖች፣ ምቹ መንገድ፣ ደረጃውን የጠበቀ የኮንቴነር ማራገፊያ ቦታ፣ ለቢሮ አገልግሎት የሚሆኑ ቢሮዎች የሚኖረው ሲሆን፤ በአይሲቲ ቴክኖሎጂ የሚደራጅ ዓለማቀፋዊ መመዘኛዎችን አሟልቶ እየተገነባ የሚገኝ የአገሪቱ ትልቁ የሎጂስቲክስ ማዕከል እንደሚሆን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

የሞጆ ደረቅ ወደብ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ከዓለም ባንክ በተገኘ 150 ሚሊዮን ዶላር ብድር እና በኢትዮጵያ መንግስት የሚገነባ የኢትዮጵያን ቀጣይ የልማትና ዕድገት ጎዞን የሚያሳልጥ የሎጂስቲክስ ማዕከል እንሚሆንም ይታወቃል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here