ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ በአስር ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንድትለቀቅ አዘዘ

0
1169

ማክሰኞ ግንቦት 30 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) “ሮሃ ሚዲያ” የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና ባለቤት መዓዛ መሐመድ በአስር ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንድትለቀቅ በፍርድ ቤት ተወሰነ።

የመዓዛን የዋስትና ጥያቄ ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 30 ቀን 2014 የፈቀደው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

መዓዛ ከጓደኛዋ መኖሪያ ቤት በፖሊስ የተያዘችው ከአስር ቀናት በፊት ግንቦት 20 ቀን 2014 ነበር።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here