10 ዲጂታል ቴክኖሎጂን የመቀበልና የመጠቀም አቅም ያላቸው አገራት

0
1143

ምንጭ፡-ስታቲስታ (2022)

ኢትዮጵያ በንጉሥ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት የተለያዩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ስትተዋወቅ፣ ቴክኖሎጂዎቹ ተቀባይነት ለማግኘት ብዙ ጊዜ ፈጅቶባቸው ነበር። የክፉ አሠራር መግቢያ ነው ተብሎ ስልክን ጨምሮ ብዙ የተነቀፉና በስጋት ይታዩ የነበሩ ቴክኖሎጂዎች ነበሩ። ‹ሰይጣን ቤት› እየተባለ የሚጠራው አዲስ አበባ ፒያሳ የሚገኘው የመጀመሪያው ሲኒማ ቤት እንኳ ለዚህ ምስክር ነው። ዛሬ ነገሮች ተቀይረዋል። ምንም እንኳ ጊዜ የሚወስድ ቢሆንም፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ዓለምን በተዋወቁበት ቅጽበት ኢትዮጵያም ይደርሳሉ።
ስታቲስታ ባወጣው ዝርዝር መሠረት፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂን በመቀበልና በመጠቀም በኩል፣ ከዓለም አገራት ሁሉ አሜሪካ ፍጽምት ለመባል ምንም የማይቀራት ሆና በአንደኝነት ተቀምጣለች። በዚህ 63 አገራት በተቀመጡበት ዝርዝር ውስጥ የተካተቱት አፍሪካዊ አገራት ደቡብ አፍሪካ እና ቦትስዋና ብቻ ሲሆኑ፣ ደረጃቸውም በዝርዝሩ ከመጨረሻዎቹ ተርታ ነው።


ቅጽ 4 ቁጥር 188 ሰኔ 4 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here