የግመል ግልቢያ ውድድር በድሬዳዋ ተካሒዷል

0
537

በመከካለኛው ምስራቅ እና አልፎ አልፎም በሩቅ ምስራቅና በደቡባዊ የእስያ አገራት የሚዘወተረው የግመል ግልቢያ በመስራቃዊቷ የኢትዮጵያ ክፍል ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተከናውኗል። በኢትዮጵያ እምብዛም ባይለመድም ዕሁድ መስከረም 18/2012 የተካሔደው የግመል ግልቢያ ውድድሩ በርካቶች እንደታደሙት አዲስ ማለዳ አረጋግጣለች።

ለ32ኛ ጊዜ በድሬዳዋ እየተከበረ የሚገኘውን ዓለም የቱሪዝም ቀን አስመልክቶ የተከናወነው የግመል ግልቢያ ውድድር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና ዘርፉን በማሳደግ ከፍተኛ የጎብኝዎች መስህብ ማድረግ እንደሚቻልም ኢፌዲሪ የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ሒሩት ካሳው (ዶ/ር) አስታውቀዋል። በተለይ በአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ ዘንድ የግመል ሃብት በስፋት መኖሩን ከግምት ውስጥ በማስገባት  የግመል ውድድርን ባህል አድርጎ በመጠቀም እንዲለመድ፣እያደገና ኦየጎለበተ እንዲሄድ በኹሉም የባድርሻ አካላት ጥረት መኖር እንዳለበትም በበዓሉ ላይ ተገልጿል። በሦስት ዙር በተካሔደው የግመል ውድድር ሱፍያን መሀመድ፣አህመድ ኢብራሂምና መሐመድ ቶፊቅ የተባሉ ተወዳዳሪዎች ከአንድ እስከ ሦስት የወጡ ሲሆን ለአሸናፊዎችም ምስክር ወረቀትና የማበረታቻ ገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

” ቱሪዝም ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለተሻለ ሕይወት” በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የዓለም የቱሪዝም ቀን በድሬዳዋ እንደቀጠለ ነው።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here