ከሃምሳ ዓመታት በላይ በስራ ላይ የቆየው የወንጀለኛ መቅጫ ማሻሻያው ተጠናቆ ለሚንስትሮች ምክር ቤት ቀረበ

0
979

ከግማሽ ምዕተ ዓመት  በላይ በስራ ላይ የቆየው የወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ሕግ የማስረጃ ጉዳዮችን እንዲያካትት እና በ1996 ዓ.ም ከወጣው የወንጀል ሕግ ጋር ስያሜው እንዲጣጣም ተደርጎ ሲሻሻል የነበረው ረቂቅ ተጠናቆ፤ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀረበ።

በኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕግ ጥናት ማርቀቅና ማስረጽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት  በላይሁን ይርጋ እንደገለፁት  ረቂቁ « የወንጀል ሕግ ስነ-ስርዓትና የማስረጃ ሕግ» የሚል ስያሜ ተሰጥቶት በ444 አንቀጾች ተቀርጾና በርካታ ከዘመኑ ጋር የሚሄዱ አዳዲስ ጽንሰ ሃሳቦች ተካተውበት እንዲሁም የነበሩት ድንጋጌዎች አሁን ካለው የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ስርዓት ጋር አብረው እንዲሄዱ ተደርገው መሻሻላቸውን አስረደድተዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አያይዘውም አዳዲስ ከተጨመሩት ፅንሰ ሀሳቦች መካከል ለአብነት የጠቀሱ ሲሆን እነዚህም የጥፋተኝነት ድርድር ማለትም በዐቃቤ ህግና በተከሳሽ መካከል ተከሳሽ ጥፋተኛነቱን በሚያምንበት ጊዜ በዐቃቤ ህግ በኩል የቅጣት መጠን ወይም የክስ ብዛትን ለመቀነስ የሚደረግ ስምምነትን በተመለከተ ረቂቁ ላይ የተቀመጠ ሲሆን በተጨማሪም የመጨረሻ ፍርድን እንደገና ስለማየት (Review of Judgment) ይህ ሲባል አንድ የወንጀል ጉዳይ ላይ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ ጉዳዩን እንደገና የማየት እንዲሁም ከዚህ በፊት የህግ ማዕቀፍ ያልነበረው በወንጀል ጉዳይ አለማቀፍ ትብብርና የሞት ፍርድ አፈጻጸምን በተመለከተ ውሳኔ ከተሰጠ ጀምሮ ከተቀመጠለት ከሁለት አመት በላይ ከቆየ ወደ እድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንደሚቀየር በረቂቁ ላይ ተሻሽሎ መቀመጡን  በላይሁን ገልጸዋል፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here