የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ አፈፃፀም መርሃ ግብር ተቀይሯል

0
431

የሲዳማ ክልልነት ጥያቄን ተከትሎ ሕዝበ ውሳኔ ለማካሔድ የታሰበ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በዚህም መሰረት ለቅስቀሳ ተይዞለት የነበረው መርሃ ግብር ከመስከረም 18 እስከ 22/2012 ቢሆንም ከጥቅምት 18 እስከ 22/2012 እንዲዛወር ተደርጓል። ከዚህ ቀደም ተይዞለት የነበረው መርሃ ግብር እንዲዛወሩ የተደረገበት ምክንያትም የቅስቀሳ ስራው መራጮች ምዝገባ ከሚደረግበት ጊዜ ጋር በመቀራረቡ እንደሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ቦርዱ በአፈፃፀም ጉዳዮች የተነሳ የሚኖሩ ቀናት ለውጥና መሸጋሸጎችን ለወደፊትም ይፋ እንደሚያደርግ ግልፅ አድርጓል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባሳለፍነው ሳምንት የሲዳማ ክልልነት ጥያቄን መሰረት አድርጎ ለሚካሔደው ሕዝባዊ ውሳኔ ኹለት ምርጫ ምልክቶችን ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው። የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ በመጪው ኅዳር 3/2012 ላይ እንደሚከወንም ቀን ተቆርጦለታል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here