- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 3ሽሕ ዘመናዊ አውቶብሶችን ከውጪ በማስመጣት በከተማዋ ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመፍታት እየሰራ እንደሆነ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ አስታውቀዋል። (አዲስ ማለዳ)
……………………………………………………………………………
- በሰሜን ጎንደር ዞን ጭልጋ እና አካባቢው የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ግጭቱ እንዳይበርድ የሚፈልጉ አካላት እንዳሉና የመገናኛ ብዙሀንም እንደሚገኙበት እና ከዚህም ጥፋታቸው እንዲቆጠቡ የአማራ ክልል የሰላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ አገኘሁ ተሻገር አሳስበዋል። (አዲስ ማለዳ)
………………………………………………………………………
- ሳይንሳዊ፣ ቴክኒካዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ እና የንግድ ትብብር ላይ አተኩሮ የሚወያየው ሰባተኛው የኢትዮ-ሩሲያ የጋራ ኮሚሽን ጉባኤ በሩሲያ ፒተርስበርግ እየተካሔደ ነው። (አዲስ ማለዳ)
………………………………………………………………….
- በአፋር ክልል ሰርዶ 2ሽሕ ሰዎችን የንፁህ ውሃ ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለው እና በዓይነቱ የመጀመሪያ ሆነው ቀጣይነት ያለው የውሃ ፕሮጀክት በአሜሪካ መንግስት ድጋፍ ተገንብቶ ተመረቀ። (አዲስ ማለዳ)
…………………………………………………………
- አሜሪካ ከፈረንጆች 2007 ጀምሮ የወባ በሽታን ለመቆጣጠር በሚል 442 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ መለገሷን በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሬይነር አስታወቁ። ”ወባን ማስወገድ ከእኔ ይጀምራል” በሚል መሪ ቃል አዲስ ዘመቻም ተጀምሯል። (አዲስ ማለዳ)
………………………………………………………………………………
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ተጨማሪ የፌዴራል መንግስት የስራ ቋንቋዎች እንዲኖሩ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ ገለጹ፡፡ (ኦቢኤን)
……………………………………………………………………
- የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባወጣዉ አስቸኳይ ማሳሰቢያ በ17ኛዉ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፉ ኹሉም የማራቶን ሯጮች እስከ ሦስት ወር ድረስ በየትኛዉም የዓለም አቀፍ ዉድድሮች ላይ እንዳይሳተፉ ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡ (አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ)
…………………………………………………………………………….
- በአዲስ አበባ ከተማ የፍል ውሃና አካባቢው የልማት ተነሺዎች ለ13 ዓመታት ሲያነሱት የነበረው የይዞታ ማረጋገጫ ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱ ተገለፀ። (ፋና ብሮድካስቲንግ)



