የደቡብ ሱዳን ተፎካካሪ ቡድን መሪ ሪክ ማቻር በቀጣዩ ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ

0
453

የቀድሞው የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዘዳንትና የአሁኑ የተፎካካሪ ፓርቲ መሪ ሪክ ማቻር (ዶ/ር) በቀጣዩ ሳምንት ወደ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት  አዲስ አበባ እንደሚመጡ ታወቀ። ለልዩ ስብሰባ በመጪው ሳምንት አዲስ አበባ ላይ የሚከትሙት ሪክ ማቻር በኅዳር 2012 እንዲካሔድ ቀን ከተቆረጠለት የሽግግር መንግስት አስቀድመው መምጣታቸው ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ደቡብ ሱዳን የዜና አገልግሎት የአገሪቱን አንድ ከፍተኛ የጦር ባለስልጣን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

የዜና አገልግሎቱ እንደዘገበው፤ ከአዲስ አበባው ልዩ ስብሰባ በኋላ ሪክ ማቻር ከደቡብ ሱዳን ፕሬዘዳንት ሳልቫ ኪር ጋር በጁባ ተገናኝተው ፊት ለፊት ተገናኝተውእንደሚወያዩ ይጠበቃል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here