መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናሃይኒከን ኢትዮጵያ "ብርታት" የተሰኘ አዲስ ከአልኮል ነፃ መጠጥ ወደ ገበያ ማስገባቱን አስታወቀ

ሃይኒከን ኢትዮጵያ “ብርታት” የተሰኘ አዲስ ከአልኮል ነፃ መጠጥ ወደ ገበያ ማስገባቱን አስታወቀ

ማክሰኞ 14 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ሃይኒከን ኢትዮጵያ “ብርታት” የተሰኘ አዲስ ከአልኮል ነፃ ሀይል ሰጪ መጠጥ ወደ ገበያ ማስገባቱን በዛሬው ዕለት አስታውቋል።

”ብርታት“ የተሰኘው ከአልኮል ነፃ መጠጥ ከሌሎች የአልኮል ነፃ መጠጦች የሚለየው ብርታት ሰጪ በመሆኑ ነው ያሉት፤ በሃይኒከን ኢትዮጵያ የ“ብርታት” ከአልኮል ነፃ መጠጥ የብራንድ ማናጀር ሎራ ጆን ሲሆኑ፤ በተጨማሪም ብርታት ከገብስ የተጠመቀ በመሆኑ ተፈጥሮአዊነቱ በጠበቀ መልኩ ለጤና ተስማሚ ሆኖ ለህብረተሰቡ መቅረቡን ተናግረዋል።

”ብርታት“ ከአልኮል ነፃ መጠጥ ከሌሎች ከአልኮል ነፃ መጠጦች ጋር እኩል በሆነ ዋጋ ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ እና በሃዋሳ ከተማ ለገበያ እንደሚቀርብ የተናገሩት ሎራ፤ በቀጣይ ኹለት እና ሦስት ወራት ውስጥም በሌሎች ከተሞች ምርቱን የማዳረስ ሥራ እንደሚሰራ ለአዲስ ማለዳ አስረድተዋል።

”ብርታት“ ከአልኮል ነፃ መጠጥ እንደ ብራንድ የቆመው ለማይደክሙና፤ ያሰቡትን ማሳካት ወደፊት ለሚጓዙ መሆኑ የተነገ ሲሆን፤ ለዚህም “ወይ ፍንክች” የሚል መለያ እንደተሰጠውም ተገልጿል።

ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች