መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናኬሪያ ኢብራሒም እና አሰፉ ሊላይ በማረሚያ ቤት ውስጥ ከወንዶች ዕኩል መብታቸው እንዲከበር...

ኬሪያ ኢብራሒም እና አሰፉ ሊላይ በማረሚያ ቤት ውስጥ ከወንዶች ዕኩል መብታቸው እንዲከበር አቤታታ አቀረቡ

ሰኞ ሰኔ 13 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዬ ኬሪያ ኢብራሒም እና የቀድሞ የትግራይ ክልል የገቢዎች ቢሮ ሀላፊ አሰፉ ሊላይ በማረሚያ ቤት ውስጥ ከወንዶች ዕኩል መብታቸው እንዲከበር አቤታታ አቀረቡ።

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በሽብር ወንጀል የተከሰሱት በእነ ዶ/ር ደብረጺኦን ገ/ሚካኤል የክስ መዝገብ የተካተቱ የ17 ተከሳሾችን ጉዳይ ተመልክቷል።

ኬሪያ ኢብራሒም፣ ዶ/ር አብርሐም ተከስተ፣ ዶ/ር አዲስአለም ባሌማ እና ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔን ጨምሮ 17 ተከሳሾች ከጠበቃ ዘራይ ወልደሰንበት ጋር ተገኝተዋል።

በክስ መዝገቡ የተካተቱ ሦስት ድርጅቶች ማለትም የትራንስ ኢትዮጲያ፣ የሱር ኮንስትራክሽን እና የመስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪግን በቀረበባቸው የሽብር ወንጀል ክስ በተመለከተ የክስ መቃወሚያ በጽሁፍ አቅርበዋል።

በዚህ የክስ መቃወሚያ ጦርነቱ የዕርስ በዕርስ ጦርነት የሚባል በመሆኑ በዚህ ጦርነት የተሳተፉ ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰብ በማንኛውም ወንጀል ሊከሰስም ሆነ ሊቀጣ የማይችል ስለመሆኑ ዘርዝረው ጠበቃ ዘራይ ወልደሰንበት 20 ገጽ የክስ መቃወሚያ ለችሎቱ እና ለከሳሽ ዓቃቢህግ እንዲደርሰው አድርገዋል።

ከሰኔ 28 በኋላ ዓቃቢህግ የድርጅቶቹ የክስ መቃወሚያ ላይ መልስ አቅርብ ተብሏል።

ሌላኛው ተከሳሽ ካሌብ ኦይል ኢትዮጵያ ለትግራይ ማዕከላዊ ወታደራዊ ኮማንድ የተሽከርካሪ ድጋፍ በማድረግ የተዘረፈ ነዳጅ በ83 የነዳጅ ቦቲ መኪና በመጫንና በማጎጎዝ ድጋፍ በማድረግ ወንጀል የቀረበት ክስ በችሎት በንባብ ተሰምቷል።

የካሌብ ኢትዮጲያ ጠበቃ ደስታ በርሔ ክሱ ግልጽ መሆኑን ያረጋገጡ ሲሆን፤ በኹለት ሳምንት ውስጥ የክስ መቃወሚያ እንደሚያቀርቡ ለችሎቱ ገልጸዋል።

በትግራይ ክልል በተከናወነ ኢ- ህገመንግስታዊ ምርጫ ተሳትፈዋል ተብለው የተከሰሱት የቀድሞ የአሲንባ ፖለቲካ ፖርቲ አስተባባሪ ዶሪ አስገዶም የክስ ጉዳያቸው ከክስ መዝገቡ ተነጥሎ ለብቻ እንዲታይላቸው አመልክተዋል።

በባለፈው ቀጠሮ ለምርመራ ተይዞባቸው የነበረ የግል ስልክ እንዲመለስላቸው ታዞ የነበረው ትዕዛዝ እንዳልተፈጸመ ገልጸዋል።

በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ሀላፊዎች በኩል ስልኬ እንዲመለስልኝ የፈቀዱ ቢሆንም፤ የንብረት ክፍል ሃላፊ ግን ተወካዬ ሊወርድ ሲሄድ ባለቤቱ በአካል መጥቶ የእጅ አሻራ ተነስቶ ነው መውሰድ ያለበት ብለው እንደመለሱት ለፍርድ ቤቱ ገልጸው አቤቱታ አቅርበዋል።

ፍርድ ቤቱም የባለፈው የችሎቱ ትዕዛዝ ተፈጽሞ ማየት ያስፈልጋል ሲል በቀጣይ ቀጠሮ የንብረት ክፍል ሃላፊ ስልኩን ይዞ በችሎት እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰቷል።

ዶሪ አስገዶም ክሴ ለብቻዬ ተነጥሎ ይታይልኝ ሲሉ ያቀረቡትን አቤቱታን በተመለከተ ደግሞ፤ ከሳሽ ዓቃቢህግ ሰኔ 28 ቀን አስተያየት እንዲሰጥበት ታዟል።

ይህ በእንዲህ እያለ የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዬ ኬሪያ ኢብራሒም እና የቀድሞ የትግራይ ክልል የገቢዎች ቢሮ ሀላፊ አሰፉ ሊላይ ከወንዶች ዕኩል መብታቸው እንዲከበር ጠይቀዋል።

በሴቶች ማረሚያ ቤት ከወንዶች በተለየ የአሰራርና የመመሪያ ልዩነት አለ ሲሉ ገልጸዋል።

ወንዶች ተከሳሾች በየቀኑ ስልክ እንዲደውሉ እንደሚደረግ የጠቀሱት ኬሪያ በሴቶች ማረሚያ ቤት በኩል ግን ስልክ ለመደወል የሚፈቀድልን በሳምን ወይም በኹለት ሳምንት አንድ ጊዜ ለ5 ደቂቃ ብቻ ነው ሲሉ አብራርተዋል።

- ይከተሉን -Social Media

የምትደውሉበት ጉዳይ ተጣርቶ ነው የምትደውሉት እንባላለን ያሉት ኬሪያ ሲፈልጉ ይነፍጉናል፤ ሲፈልጉ ያስደውሉናል ስለዚህ የጾታ ልዩነት ሳይደረግብን እኩል ልንገለገል ይገባል ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል።

ለ 30 ደቂቃ ከቤተሰቦቻችን ጋር በስልክ ለማውራት ይፈቀድልን ሲሉም ችሎቱን መጠየቃቸውን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱና ዘግባለች።

ፍርድ ቤቱ በቀጣይ ቀጠሮ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥበት ትዕዛዝ መስጠቱ ታውቋል።

ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች