መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናተመድ በምዕራብ ወለጋ ቶሌ ቀበሌ የተገደሉ ንጹሃንን በተመለከተ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ጠየቀ

ተመድ በምዕራብ ወለጋ ቶሌ ቀበሌ የተገደሉ ንጹሃንን በተመለከተ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ጠየቀ

ሐሙስ ሰኔ 16 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን በምዕራብ ወለጋ ቶሌ ቀበሌ የተፈፀመውን አሰቃቂ የጅምላ ግድያ በተመለከተ በገለልተኛ ወገን የማጣራት ሥራ እንዲሰራ ጠይቋል፡፡

የድርጅቱ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ሚሼል ባችሌት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ አውጥተዋል።

ኮሚሽነር ባችሌት በመግለጫቸው ባሳለፍነው ቅዳሜ በኦሮሚያ ክልል በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን የተገደሉበት ጥቃት በገለልተኛ ወገን እንዲጣራና አስፈላጊው ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

ኮሚሽነሯ በአካባቢው ያሉ የአይን እማኞችን፣ ከግድያ የተረፉ ሰዎችን እና ሌሎች መረጃዎችን እንደሰበሰበ ገልፀው፤ ግድያው የተፈጸመው የአማራ ተወላጆች በሚኖሩበት በጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ እንደሆነ መረጋገጡን ተናግረዋል።

በዚህም ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃንን እንደተገደሉ ተረጋግጧል ያሉት ኮሚሽነሯ፤ የግድያው ዋንኛ ሰለባዎችም ሴቶችና ህፃናት መሆናቸውን በመግለፅ፤ ከግድያው የተረፉ ከ2 ሺህ በላይ ዜጎች መኖሪያ ቀዬአቸውን ለቀው መሰደዳቸውንም ገልፀዋል።

ኮሚሽነሯ ጥቃቱ እጅግ በጣም አሰቃቂ እንደሆነ ገልፀው፤ የኢትዮጵያ መንግስት በገለልተኛ አካል ጉዳዩን በማጣራት የዜጎችን የመኖር መብት እንዲያስከብርም ጠይቀዋል፡፡

በተጨማሪም በቁጥር ምን ያህል እንደሆኑ ያልታወቁ ሰዎች አድራሻቸው መጥፋቱንም ገልፀው፤ መንግስት ህግ የማስከበር ሥራውን እንዲሰራ እና የታገቱ ዜጎችን እንዲያስለቅቅ አሳስበዋል፡፡

ጉዳዩ በህጋዊ መንገድ ተጣርቶ የተሰወሩ ሰዎች የት እንዳሉ እንዲረጋገጥ የጠየቀው ድርጅቱ፤ መንግድት የዜጎችን ነፃነትና ደህንነትም ሊያስጠብቅ እንደሚገባ አሳስቧል።

በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች በሚከሰቱ ግጭቶች ንጹሃን ሰለባ እየሆኑ መሆኑን የተናገረው ድርጅቱ መንግስት የዜጎችን ደህንነት ሊያረጋግጥ ይገባልም ብሏል፡፡

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች