መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ያወጣውን መግለጫ ውድቅ አደረገች

ኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ያወጣውን መግለጫ ውድቅ አደረገች

ህብረቱ ለግብጽ ወግኖ ያወጣውን መግለጫ ድጋሚ እንዲያጤነውም ጠይቃለች

ሐሙስ ሰኔ 16 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ያወጣውን መግለጫ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አስታወቀች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ መግለጫ ሰጥተዋል።

ቃል አቀባዩ በዚህ ጊዜ እንዳሉት ከሰሞኑ የአውሮፓ ህብረት እና ግብጽ በጋራ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ባወጡት መግለጫ ዙሪያ አስተያየት ሰጥተዋል።

አውሮፓ ህብረት በእስካሁኑ የህዳሴው ግድብ የሦስትዮሽ ውይይቱ ላይ ታዛቢ ነበር ያሉት አምባሳደር ዲና፤ የሰሞኑ አስተያየት ግን ውግንናውን ለግብጽ በሚመስል መንገድ መግለጫ ሰጥቷል ብለዋል።

የአውሮፓ ህብረት ከግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በመሆን የግብጽ ታሪካዊ የውሃ ድርሻ ሊነካ አይገባም ብሏል።

ይህ አስተያየት ከአንድ የድርድሩ ታዛቢ አካል መሰጠቱ ውግንናው ላይ ጥያቄ እንድናነሳ አስገድዶናል ያሉት አምባሳደር ዲና፤ ህብረቱ ከግብጽ ጎን ወግኖ የሰጠውን አስተያየት መልሶ እንዲያጤነው እንጠይቃለንም ማለታቸውን አል አይን ዘግቧል።

በኢትዮጵያውያን እና መንግስት ወጪ እየተገነባ ያለው ታላቁ የህዳሴው ግድብ ግንባታ 84 በመቶ መጠናቀቁ ይታወሳል።

ግንባታው በዚህ ደረጃ ላይ እያለም ከግድቡ ኹለት ተርባይኖች 700 ሜጋ ዋት ሀይል እንዲያመነጩ ለማድረግ በተደረገው ጥረት ከሦስት ወራት በፊት አንዱን ተርባይን ወደ ሥራ በማስገባት 350 ሜጋ ዋት ሀይል ማመንጨት መጀመሩም አይዘነጋም።

ሦስተኛው የህዳሴው ግድብ ውሀ ሙሌት በሚቀጥለው ወር እንደሚጀመር መንግስት ከዚህ በፊት በሰጣቸው መግለጫ መናገሩ ይታወቃል።

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች