የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽኅፈት ቤት በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ክፍለ ከተማ ዘመናዊ የኢንዱስትሪ መንደር በ93 ሄክታር መሬት ላይ ለመገንባት ማቀዱን አስታወቀ።
በዘንድሮው ዓመት በ42 ነጥብ 6 ሄክታር መሬት ላይ የኢንዱስትሪ መንደር ግንባታውን ለመጀመር የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎችን በማጠናቀቅ ወደ ተግባር እየተገባ መሆኑን ጠቁሟል።
ፕሮጀክቱ የከተማው አስተዳደር ግዙፍ የልማት ዕቅዶች አካል ሲሆን፣ የኢንተርፕራይዞች የሽግግር ማሳለጫ በመሆንም ለከተማዋ ጉልህ ጠቀሜታ ለማበርከት ታልሞ እንደሚሰራም የከንቲባ ጽህፈት ቤቱ አመላክቷል።
እስካሁን በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስት የሚተዳደሩ የኢንዱስትሪ መንደሮች እንጂ መዲናዋ የምታስተዳድረው የራሷ የኢንዱስትሪ መንደር ያልነበራት በመሆኑ፣ ከዚህ በኋላ አዲስ አበባ በክላስተር የለሙና ሼድ የተገነባላቸው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ይኖሯታል ተብሏል።
ቅጽ 4 ቁጥር 190 ሰኔ 18 2014



