የሂልተን ሆቴል ይዞታ 70 በመቶ ወደ ግል ሊዘዋወር ነው

0
674

የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በ 2012 በጀት ዓመት ሂልተን ሆቴልን 70 በመቶ ድርሻ ወደ ግል ይዞታ ለማዘዋወር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን፣ የሆቴሉ የሀብት ግመታ ጥናት እንደተረጋገጠም በሚወጣ ጨረታ ድርሻው እንደሚዘዋወር የኤጀንሲው ዳይሬክተር ጄነራል በየነ ገ/መስቀል ባሳለፍነው ሳምንት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

በዓለም አቀፉ የሂልተን ባለቅርንጫፍ ሆቴሎች አስተዳደር ስር የሆነውና ንብረትነቱ በኢትዮጵያ መንግስት ባለቤትነት የተያዘው ሂልተን ሆቴል ለገበያ እንደሚቀርብ ለአመታት ቢነገርም ቀን ግን ሳይቆረጥለት ቆይቷል። ከዚህ በተጨማሪም በፍል ውሃ አገልግሎት ድርጅት ስር ላንጋኖ የሚገኘው ሆቴል እንዲሁም ሶስት የማኑፋክቸሪንግና ስድስት የስኳር ፋብሪካዎች በዚህ ዓመት ወደ ግል ይዞታ እንደሚተላለፉ ዳይሬክተሩ ጨምረው አስታውቀዋል።

በ2011 እንደ አዲስ የተዋቀረው የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ አሁን በስሩ 23 የልማት ድርጅቶችን የያዘ ሲሆን፣ በዚህ ዓመትም አዶላ ወርቅና የመንግስት ነዳጅና ባዮፊዩል ኮርፖሬሽን ተዋህደው ቁጥሩ ወደ 21 ዝቅ እንደሚል ተገልፃል።

ቅጽ 1 ቁጥር 48 መስከረም 24 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here